የተያዙ የኮንትሮባንድ እቃዎች በግልጽና በሐራጅ ጨረታ መሸጥ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 13/12/2018 እና 16/12/18 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም ለአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባለበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ስልክ ቁጥር 022 224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የጨረታ መስፈርቶች
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 13/12/2018 እና 16/12/2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ፡፡
- ግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።
| ተ.ቁ | የጨረታ ቦታ | የጨረታው ዓይነት | ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች | የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ | የጨረታው የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት |
| 1 | ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት | ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ | ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ ፥ የሞባይል ቀፎና አከሰሰሪ፥ ኤሌክትሮኒከስ፥ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት፥ ኮስሞቲከስ፣ መነፅር፣ ጌጣገጥ፥የሳሙና ፋብርካ አካልማሽነሪ፥ መሰላልብረቶችእና ሌሎችልዩ ልዩ እቃዎች | የግልጽና የሐራጅ ጨረታ 13/12/2018 እና 16/12/2018 ዓ.ም እስከ 3፡45 | ለግልጽና የሐራጅ 13/12/2018 እና16/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ4፡00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያጊዜ 13/12/2018 እና16/12/2018 እና16/12/2018ዓ.ም 5፡00ሰዓት ይሆናል። |
- የጨረታ መከፈቻ ቦታ: በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለቡት ወይም በታዛቢዎች ይከፈታል።
- በጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዘን ማውጣት ይኖርበታል።
- ከላይ በተ.ቁ7 በተገለጹት ቀናት ወስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች በጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Awash Customs Branch Office sells seized contraband items—shoes, clothes, car parts, phones, electronics, food, sports goods, watches, cosmetics, glasses, decorations, soap factory parts, ladders, etc.—via open and auction tender at Kaliti. Bidders need renewed trade license, VAT registration
(This answer was cut short — ask a more specific question to get the rest.)
