የተወረሱ አዳዲስ አልባሳት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኮስሞቲክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ እቃዎች)፣ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ የእይታ መሣሪያዎች (መነጽር)፣ የተሽከርካሪ ጐማዎች፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተርሳይከሎችን በግልጽ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ
የጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ ጨረታ ቁጥር ግ-04/2018/19 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ አዳዲስ አልባሳት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኮስሞቲክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ እቃዎች)፣ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ የእይታ መሣሪያዎች (መነጽር)፣ የተሽከርካሪ ጐማዎች፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተርሳይከሎችን በግልጽ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦከሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
- ለጨረታ በቀረቡት እቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው እቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስከር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦከሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመከፈል ከኦከሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላል፡፡
- በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖሩም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ እቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
- በጨረታው የወጡትን ሞተር ሳይከሎች ማንኛውም እድሜው ከ8 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟላ በቀበሌ መታወቂያ ብቻ መጫረት ይችላል፡፡
| ተ.ቁ | የእቃው ዓይነት | የጨረታው ዓይነት | በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን | የሚካሄድበት ቀን | ጨረታው የሚዘጋበት ሰዓት | ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት | ስልክ ቁጥር |
| 1 | አዳዲስ አልባሳት | ግልጽ | 08/12/2018 | 15/12/2018 | 4:00 | 8:00 | 022-111-84-29 022-211-89-25 |
| 2 | የኤሌክትሮኒክስ | ግልጽ | 08/12/2018 | 15/12/2018 | 4:00 | 8:00 | |
| 3 | ኮስሞቲክስ | ግልጽ | 08/12/2018 | 15/12/2018 | 4:00 | 8:00 | |
| 4 | ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች | ግልጽ | 08/12/2018 | 15/12/2018 | 4:00 | 8:00 | |
| 5 | ሸቀጣሸቀጥ /ልዩ ልዩ/ | ግልጽ | 08/12/2018 | 15/12/2018 | 4:00 | 8:00 | |
| 6 | ኮንስትራክሽን ማቴሪያል | ግልጽ | 08/12/2018 | 15/12/2018 | 4:00 | 8:00 | |
| 7 | የእይታ መሣሪያዎች/መነጽር/ | ግልጽ | 08/12/2018 | 15/12/2018 | 4:00 | 8:00 | |
| 8 | የቢሮ መገልገያ | ግልጽ | 08/12/2018 | 15/12/2018 | 4:00 | 8:00 | |
| 9 | ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን | ግልጽ | 08/12/2018 | 15/12/2018 | 4:00 | 8:00 | |
| 10 | የተሽከርካሪ ጐማዎች | ግልጽ | 08/12/2018 | 15/12/2018 | 4:00 | 8:00 |
- የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የእቃዎቹን ዝርዝር፥ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦከሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ኦከሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡
- በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (Customs Commission Adama Branch Office) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ በማሰራት በኦንላይን ወይም በአካል ወደ ኦከሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
- በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡ ነገር ግን በጨረታው ተሳትፈው ቢገኙ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
- በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ ስለሚገኙ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፣ ለተሸናፊ ተጫራቶች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለጸ በ3 /ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 9 ላይ በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈጸመው ባሉበት ሁኔታ ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡
የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/011 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ- የአዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 0221118429 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት
