Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ጀሞ ለቡ ወረዳ 1 አካባቢ በሚገኘው የክለቡ የተጫዋቾች የመኖሪያ ካምፕ ቅጥር ግቢ ውስጥ ጥራቱን የጠበቀ ለጤና ተስማሚ የሆኑ ምግቦችን በተመጣጣኝ ዋጋ የምግብ አቅራቢ ድርጅቶችን ከእነ እቃው በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡


የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ጀሞ ለቡ ወረዳ 1 አካባቢ በሚገኘው የክለቡ የተጫዋቾች የመኖሪያ ካምፕ ቅጥር ግቢ ውስጥ ጥራቱን የጠበቀ ለጤና ተስማሚ የሆኑ ምግቦችን በተመጣጣኝ ዋጋ የምግብ አቅራቢ ድርጅቶችን ከእነ እቃው በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም

  • በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም (TOT) ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
  • በመንግስታዊ እና በግል ተቋማት ላይ የሰሩበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ለስፖርተኛ የሚሆኑ ምግቦችን ጠንቅቀው የሚያውቁ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 300,000 ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም
  • ክለቡ ከአዲስ አበባ ውጭ ለአንድ ወር እና ከዚያ በላይ በክልል ከተሞች ውድድር ሲኖረው በምንከራየው ገስት ሀውስ ውስጥ ከአዲስ አበባ ወደ ስፍራው በመሄድ ለስፖርተኞቹ ምግብ ለማዘጋጀት ፈቃደኛ የሆኑ በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የመመገቢያ አደራሹን እና የምግብ ማብሰያ ቁሳቁሶችን በተመለከተ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀናት ጀሞ ወረዳ 1 ትራኮን ሪልስቴት አጠገብ በሚገኘው የክለቡ የተጫዋቾች መኖሪያ ካምፕ በአካል ቀርበው መመልከት ይችላሉ፡፡
  • ማንኛውም በጨረታው ተሳታፊ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን ሜክሲኮ ቡናና ሻይ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 114 በመሄድ የማይመለስ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በመግዛት ከነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሰጥን ውስጥ የምግቡን ዋጋ እና ዝርዝር ሞልቶ በማስገባት መጫረት የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  • ጨረታው ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  • ክለቡ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በ0925 22 16 85 በመደወል መረጃ መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ

Save Tender