ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫዎችና ልዩ ልዩ ዓይነት ያገለገሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ያገለገሉ ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2026/27
- ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫዎችና ልዩ ልዩ ዓይነት ያገለገሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ እና መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች መወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ስታዲየም ቅርንጫፍ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ስታዲየም ከኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ካለ ወይት የታደሠ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሠላሳ ሺ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ደብዳቤ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ዋጋው ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከፈለገ ዮርዳኖስ ትምህርት ቤት ወረድ ብሎ በሚገኘው ግቢ የባንኩ ንብረት ክፍል እና ሜክሲኮ ኬኬር ሕንጻ ፊትለፊት በሚከኘው የባንኩ ንብረት ክፍል በአካል በመቅረብ እቃዎቹን ይችላሉ፡፡
- ግልጽ ጨረታው ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች እቃዎቹ ባሉበት ቦታ በአካል በመገኘት እና እቃዎቹን በአግባቡ ተመልክተው ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ስልክ ቁጥር
0115 581204 ወይም 0115 318097 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
