የካሜራ ድሮን እና የሬድዎ መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
1. የግዥው አይነት ---ሎት 1 የካሜራ ድሮን እናሎት 2 የሬድዎ መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚድያ ከዚህ በታች የቀረቡትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ቁጥር 001/2019 በጀት ዓመት
የግዥው ዘዴ ---- ግልፅ ጨረታ በዚሁ መሰረት በጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በፊት ለሚድያ ተቋማት ማቅረቡን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ ቲን ነምበር ምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርቲፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ አዲስ አበባ በሚገኘው ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በመሄድ በ200 ብር ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ቢድ ቦንድ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ለእያንዳንዱ ሎት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚድያ ስም ሞልተው ከኦርጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባችዋል።
4. ተጫራቾች ሎት 1 የድሮን ካሜራ ሰነድ ለብቻ የቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና 2/ሁለት ኮፒ እንዲሁም የፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና 2/ሁለት ኮፒ ሎት 2 የሬድዎ መለዋወጫ ዕቃዎች የቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና 2/ሁለት ኮፒ እንዲሁም የፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና 2/ሁለት ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በትከክል መቅረብ አለበት። የኮፒ ሰነዶች በአይነትም ሆነ በብዛት ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት።
5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን 6 ኪሎ አዲስ አበባ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መግዛት ይችላሉ፡፡ ተወዳዳሪ ድርጅቶች ጨረታውን ሞልተው አዲስ አበባ በሚገኘው ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በተወከለው የሚድያው ሰራተኛ ማስረከብ አለባቸው። ጨረታውን በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት አሶሳ በሚድያው ግዥና ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ይከፈታል፡።
6. ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
7. ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፡-በስልክ ቁጥር 09 28 65 38 53፤ 09 10 00 03 29፣ 09 12 16 86 79 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ
