Tender Detail

Tender Details

  • Company Nexus 4 Empowerment and Development
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline29 Aug 2026, 12:00 AM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-08-19 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks

Nexus for Empowerment and Development (N4ED) ለፕሮግራሞቹ  አገልግሎት የሚውሉ የምግብ፣ የንጽህና፣ የቤት ውስጥ እቃዎችን እና የኪሮሽ ክር እና ለውበት ሳሎን እቃዎች ለማቅረብ ብቁ እና ፍላጎት ያላቸውን አቅራቢዎች በዝግ ጨረታ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።


N4ED/001/26

የጨረታ ማስታወቂያ

ለምግብ፣ ለንጽህና እና ለቤት ውስጥ አገልግሎት እቃዎች አቅርቦት

Nexus for Empowerment and Development (N4ED) ለፕሮግራሞቹ  አገልግሎት የሚውሉ የምግብ፣ የንጽህና፣ የቤት ውስጥ እቃዎችን እና የኪሮሽ ክር እና ለውበት ሳሎን እቃዎች ለማቅረብ ብቁ እና ፍላጎት ያላቸውን አቅራቢዎች በዝግ ጨረታ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

ምድብ 1፡ በፍጥነት የሚበላሹ የምግብ ምርቶች ሳምንታዊ አቅርቦት

ይህ የሚያካትተው፦

  • ትኩስ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች
  • የወተት ተዋጽኦዎች
  • የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች እና ሌሎች ትኩስ የምግብ ምርቶች

ተመራጭ አቅራቢው በየሳምንቱ የሚፈለጉትን እቃዎች ላፍቶ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ፣ ኮተቤ እና ወይራ ለሚገኙ የN4ED ቢሮዎች ማድረስ አለበት።

መስፈርቶች

  • ሁሉም ምርቶች ትኩስ፣ ንጹህ እና ለሰው ልጅ ፍጆታ ተስማሚ መሆን አለባቸው።
  • ከመበስበስ፣ ከብክለት፣ ከተባይ እና ከባዕድ ነገሮች ነጻ መሆን አለባቸው።
  • የመጓጓዣና የማድረሻ ወጪዎች በተጠቀሰው ዋጋ ውስጥ መካተት አለባቸው።
  • አቅራቢው በየሳምንቱ ያለማቋረጥ ማቅረብ የሚችል አቅም ሊኖረው ይገባል።

ምድብ 2፡ የማይበላሹ የምግብ ምርቶች፣ የንጽህና እቃዎች እና የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች

ይህ  የሚያካትተው፦

  • የማይበላሹ የምግብ ምርቶች
  • የግል ንጽህና እና የእንክብካቤ እቃዎች
  • የጽዳት እና የንጽህና ማስጠበቂያ እቃዎች
  • የቤት ውስጥ እና የመጠለያ ቁሳቁሶች

መስፈርቶች

  • ሁሉም ምርቶች አዲስ እና ጥራት ያላቸው መሆን አለባቸው።
  • የምግብ ምርቶች እና ሌሎች ተመሳሳይ ፍጆታ እቃዎች ቢያንስ የ12 ወራት የቀሪ የአገልግሎት ጊዜ (Shelf Life) ሊኖራቸው ይገባል።
  • ለሁሉም የንጽህና መጠበቂያ እቃዎች ሳምፕል ከጨረታ ዶክመንት ጋር አያይዘው ያስገቡ።
  • ምርቶቹ በዋና ማሸጊያቸው ውስጥ እና በትክክለኛ መለያ የታሸጉ መሆን አለባቸው።
  • የመጓጓዣና የማድረሻ ወጪዎች በተጠቀሰው ዋጋ ውስጥ መካተት አለባቸው።

የተወዳዳሪዎች መስፈርቶች

ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ አለባቸው፦

  1. በዘርፉ የሚሰራ የንግድ ፍቃድ
  2. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት
  3. የTIN ሰርተፍኬት
  4. የVAT ምዝገባ ሰርተፍኬት
  5. የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት
  6. እንደ አግባብነቱ የምግብ ደህንነት ወይም ሌሎች ተዛማጅ ፈቃዶች
  7. የድርጅቱ መግለጫ (Company Profile)
  8. ተመሳሳይ ስራዎችን የሰራበት ልምድ ማስረጃ
  9. ቢያንስ 3 የደንበኛ ማጣቀሻዎች (References)

ምድብ 3፡ ከውጪ የሚገቡ የኪሮሽ ክሮች እና የውበት ሳሎን እቃዎች አቅርቦት

ይህ የሚያካትተው፦

  • ከውጭ የሚገቡ የቦርሳ እና የሹራብ ክሮች (Imported Yarn)
  • የተለያዩ ቀለማትና መጠኖች ያላቸው ክሮች
  • ትንሽ ተንቀሳቃሽ የጸጉር ማድረቂያ (Hair Dryer)
  • የጸጉር መጠቅለያ ቪጎዲን (Curling Machine)
  • ኮምቦች፣ ብሩሾች፣ ፎጣዎች
  • የመታጠቢያ ወንበር
  • የጸጉር እንክብካቤ እና ማስተካከያ ቁሳቁሶች

መስፈርቶች

  • ሁሉም ክሮች አዲስ፣ ጥራት ያላቸው እና ለሙያዊ አጠቃቀም ተስማሚ መሆን አለባቸው።
  • የሚቀርቡ ክሮች በተለያዩ ቀለማት፣ ውፍረቶች እና ዓይነቶች ሊቀርቡ ይገባል።
  • ምርቶቹ በዋና ማሸጊያቸው ውስጥ እና በትክክለኛ መለያ የታሸጉ መሆን አለባቸው።
  • የመጓጓዣና የማድረሻ ወጪዎች በተጠቀሰው ዋጋ ውስጥ መካተት አለባቸው።
  • አቅራቢው በተፈለገው ጊዜ በተጠየቀው መጠን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

የጨረታ ሰነድ ማግኛ

ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ከN4ED ዋና ቢሮ ሳርቤት አዲስ አበባ ማግኘት ይችላሉ ወይም በኢሜይል በሚከተለው አድራሻ መጠየቅ ይችላሉ፦naomi.abera@n4ed.org

የጨረታ መዝጊያ ቀን

ጨረታው ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ይዘጋል። ዘግይተው የሚቀርቡ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

ለተጨማሪ መረጃ

ስልክ፡ 0940 070 024

N4ED ማንኛውንም ወይም ሁሉንም ጨረታዎች ያለምንም ምክንያት የመቀበል ወይም የመሰረዝ መብት አለው።

 

 

Save Tender