በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣ በኮፈሌ፣ በሀዋሳ፣ ቦንጋ፤ ነቀምት፣ ባህርዳር፣ ቻግኒ እና አሰላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ፡-
የጨረታ ማስታወቂያ
የምግብ እህልና የብጣሪ እህል ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ-ምዘአዘ/ጨሸ/01ሠነድ/2018
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣ በኮፈሌ፣ በሀዋሳ፣ ቦንጋ፤ ነቀምት፣ ባህርዳር፣ ቻግኒ እና አሰላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ፡-
1. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ።
2. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ (Seed Forest products Supply Sector) ስም የጨረታ ማስከበሪያ (Bid BOND) በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም የባንከ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሱት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወይም ከአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች የተገለፀውን መጠን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል መጫረት ይችላል፤
5. ማንኛውም ተጫራች የምግብ እህሉ እና የብጣሪ እህሉ በሚገኙበት ቅ/ጽ/ቤቶች በመገኘት አይቶ መጫረት አለበት፡፡ ይህን ሳያደርግ ዋጋ ቢያቀርብ ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የዋጋማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶማቅረብ ይጠበቅበታል።
7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
8. የምግብ እህልና የብጣሪ እህል መጠን በዚህ ጨረታ ሰነድ ላይ ከተገለፀው መጠን ሊያንስ ይችላል።
9. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል ዓይነት የሚሰጠውን ዋጋ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለበት። ጨረታው ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ሰዓት ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ ጽ/ቤት እና ከላይ በተጠቀሱት ቅ/ጽ/ቤቶች ጨረታው ይከፈታል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፦ 09-11-31-35-79
አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
