Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር
  • Address ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116733497
  • Website
  • Deadline27 Aug 2018, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/
  • opening dateነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:45
  • Categories Maintenance And Repair

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የፎቶ ኮፒ፣ እስካነር እና ኘሪንተር ጥገና አገልግሎት ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር EAC039/2018

  1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የፎቶ ኮፒ፣ እስካነር እና ኘሪንተር ጥገና አገልግሎት ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30- 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -11፡00 ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ” ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎርአግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታከስ ከሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት
    • አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ
    • እንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
    • ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት፡፡
    • በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የፎቶ ኮፒ፣ እስካነር እና ኘሪንተር ጥገና አገልግሎት ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ከፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (Unconditional) ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመከፈቻ ቀን ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4:45 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይሆናል።
  6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116676204 ፋክስ ቁጥር 0116732006 መጠቀም ይችላሉ፡፡
  8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማኅበር

✨ messages.ai_summary
Ethio Agri-CEFT PLC seeks bids for photocopier, scanner, and printer maintenance services. Bidders must hold a renewed trade license, tax ID, tax clearance, supplier registration, and VAT certificate.
Save Tender