Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline27 Aug 2018, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300 (ሦስት መቶ) የማይመለስ
  • opening dateነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Vehicle

በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ስም ተመዝግበው ድርጅቱ ሲጠቀምባቸው እና ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን እና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ የተረከባቸውን


የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ስም ተመዝግበው ድርጅቱ ሲጠቀምባቸው እና ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን እና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ የተረከባቸውን

  • ልዩ ልዩ ተሸከርካሪዎች
  • ልዩ ልዩ ጋቢናዎች በተናጠል
  • ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት
  • የ132KV underground cables በብረት ድረም የተጠቀለሉ (6) ስድስት ጥቅሎች ባለበት

በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ስም ተመዝግበው ድርጅቱ ሲጠቀምባቸው እና ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ማንኛውም የስም ማዛወሪያ፤ የጉምሩክ ቀረጥ፡ ግብር፡ ተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ወጪዎች ቢኖሩ ከፍሎ በጨረታ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሁሉ ቃሊቲ ከራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል በመሃኘት ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት Ethiopian Insurance Corporation/ ስም በተሰራ ሲፒኦ ሕጋዊ ፈቃድ ከተሰጣቸው ንግድ ባንኮች በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡

ሀ/ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ) በመከፈል ከሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል እና ለገሐር ከሚገኘው የዋና መሥሪያ ቤት ሂሳብ ከፍል ከነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓም እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡

ለ/ የዕቃ እና የተናጠል ጋቢና ማስያዣ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የዕቃ ማስያዣ ብር 1000 ነው።

ሐ/ የተሽከርካሪ ማስያዣ

የጨረታ መነሻ እስከ ብር 50,000.00 20 በመቶ
ከብር 50,001.00 እስከ ብር 100,000.00 ብር 15,000.00
ከብር 100,001.00 እስከ ብር 200,000.00 ብር 25,000.00
ከብር 200,001.00 እስከ ብር 300,000.00 ብር 37,000.00
ከብር 300,001.00 እስከ ብር 400,000.00 ብር 50,000.00
ከብር 400,001.00 እስከ ብር 500,000.00 ብር 60,000.00
ከብር 500,001.00 እስከ ብር 800,000.00 ብር 75,000.00
ከብር 800,001.00   ብር 100,000.00

ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኃላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ሂሳቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ የዙትን ንብረት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ከፍያ አጠናቀው ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። ከፍያ ፈለመው ንብረቶቹን በጨረታ ዝርዝር ሰነድ ላይ በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 3,000.00 (ሦስት ሺህ ብር) ይከፍላሉ።

ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ተሽከርካሪም ሆነ ቁሳቁስ በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ-አንድ የጨረታ ሰነድ ለአንድ ተሽከርካሪ ወይም በአንድ ጊዜ ለሚጫረት ንብረት ብቻ ተጫራቶች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት አስቀድመው በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላትና ዋናውን ሲፒኦ ከቅጂው ሲፒኦ ጋር አንድ ላይ በኢንቨሎፕ በማሸግ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለገሐር በሚገኘው በዋናው መስሪያ ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል ይከፈታል። በጨረታው ተሸናፊ የሚያገለግል ሲሆን ከአንድ በላይ መጫረት የሚፈልግ አካል በፍላጎቱ ልክ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርበታል።

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-439-25-99 እና 011-439-25-45 መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Insurance Corporation is auctioning various vehicles registered under its name, along with accident-recovered vehicles, individual cabins, vehicle parts, and 6 rolls of 132KV underground cables. Bidders can inspect items at the Recovery Technical Center and must provide bid security via CPO from licensed banks.
Save Tender