Tender Detail

Tender Details


የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 20/12/2018 እና 23/12/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 20/12/2018 እና 23/12/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የጨረታ መስፈርቶች-

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፡ የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን ከሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የመስከር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 20/12/2018 እና 23/12/2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላከሎት ማድረግ ይችላሉ፡፡
  3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5በመቶ አንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተ.ቁ የጨረታ ዓይነት ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች ለጨረታ የቀረቡ የዕቃዎች ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የጨረታ የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት
1 ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ ኤሌክትሮኒከስ፣ ምግብ ነክ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት ኮስሞቲከስ፡ መነፅር፣ ጌጣ ጌጦች የሳሙና ፋብሪካ አካል ማሽነሪ እመነበረድ ድንጋይ የተሽከርካሪ መሰላል ብረቶች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች ለግልጽ ጨረታ ለሐራጅ ጨረታ 20/12/2018 እና 23/12/2018 እስከ ጠዋቱ 3፡45 ለግልጽ ጨረታ 20/12/2018 23/12/20018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ስሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 20/12/2018 እና 23/12/2018 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
  1. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ሼዱል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡
ተ.ቁ የጨረታ ዓይነት ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች ለጨረታ የቀረቡ የዕቃዎች ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የጨረታ የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት
1 ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ ኤሌክትሮኒከስ፣ ምግብ ነክ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት ኮስሞቲከስ፡ መነፅር፣ ጌጣ ጌጦች የሳሙና ፋብሪካ አካል ማሽነሪ እመነበረድ ድንጋይ የተሽከርካሪ መሰላል ብረቶች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች ለግልጽ ጨረታ ለሐራጅ ጨረታ 20/12/2018 እና 23/12/2018 እስከ ጠዋቱ 3፡45 ለግልጽ ጨረታ 20/12/2018 23/12/20018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ስሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 20/12/2018 እና 23/12/2018 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
  1. የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል::
  2. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡
  3. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን በመረከብ ከመጋዘን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
  4. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  5. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Awash Customs Office will sell various confiscated contraband goods via open and auction tenders at Kaliti Customs Office. Items include shoes, clothing, car parts, mobile phones, electronics, food items, sports goods, watches, cosmetics, glasses, jewelry, machinery, stones, and more. Bidders need a renewed trade license, VAT registration, and tax clearance.
Save Tender