የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የስራ ክፍሎች የአልሙኒየም ፓርቲሽ እና የፋርማሲ ሼልፍ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የስራ ክፍሎች የአልሙኒየም ፓርቲሽ እና የፋርማሲ ሼልፍ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመከፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ተፈላጊ ስራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 25000 በባንክ በተመሰከረ C.P.O /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በተለያዩ ፖስታዎች በመሙላት ፋይናንሽያልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጂናልና ሁለት ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ኬዝ ቲም ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን በ08፡00 ተዘግቶ በ15ኛ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመከፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0463299263 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ
የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
✨ messages.ai_summary
Worabe Comprehensive Specialized Hospital seeks bidders to fabricate aluminium partitions and pharmacy shelves for various departments. Bidders must hold a renewed trade license, VAT registration, TIN, and supplier registration certificate.
