Automotive Supplies & Veterinary Products
የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
ሎት 1 የረዥም ጊዜ የመኪና እቃ መለዋወጫ
ሎት 2 የአጭር ጊዜ የመኪና እቃ መለዋወጫ
ሎት 3 የመኪና ጎማ
ሎት 4 የመኪና ዘይትና ቅባት
ሎት 5 የእንስሳት መድሀኒት
ከተራ ቁጥር 1-5 የተዘረዘሩትን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
2. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር ያላቸው
4. የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ /NAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይ መሆን አለባቸው፡፡
6. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋርአይይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. የጨረታው ሰነድ ከደሴ ዙ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመከፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው ከ 15 / 12 / 2018 ዓ.ም እስከ 29 /12 /2018 ዓ.ም በአየር ላይ ይውላል፡፡
10. ጨረታው በ30/12 /2018 ዓ.ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
11. ተጫራቾች ኦርጅናል እቃ መሙላትና ያሸነፉበትን እቃ በባለሙያ ማስፈተሽ አለባቸው፡፡
12. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
13. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚያቀርቡት ዕቃ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው። ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በጽ/ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት፡፡
14. ተሸናፊ ተጫራቾች በመመሪያው መሰረት ያስያዙት 2% ሲፒኦ ከአምስት ቀን በኋላ ይመለስላቸዋል፡፡
15. አሸናፊው አካል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያሲዝ ይሆናል፡፡
16. የረዥም ጊዜ የመኪና እቃ መለዋወጫ፣ አጭር ጊዜ የመኪና እቃ መለዋወጫ እና የመኪና ጎማ ግዥ እስከ በጀት አመቱ መጨረሻ ድረስ በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ግዥ እንዲፈጸምላቸው በጠየቁ ጊዜ ለማቅረብ የሚችል፡፡
17. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ በየሴክተሩ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
18. በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና ቅጂ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ እስከ 30/12/2018ዓ.ም ደሴ/ዙ/ወ/ግዥ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ እንዲያስገቡ እየገለፅን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
19. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደሴ/ዙ/ወ/ግዥ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-11-7763 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
20. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው ድርጅት/ተጫራች/ ኦርጅናል እቃ የማቅረብ ግደታ አለባቸው:፡ እንዲሁም ኢቃው ወረዳው ንብረት ከፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
ስልክ ቁጥር፡-33117763 ይደውሉ፡፡
የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
