Tender Detail

Tender Details

  • Company የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
  • Address በታርጫ ከተማ ከቴሌ ቢሮ በስተጀርባ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-04-69-39-79
  • Website
  • Deadline07 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 500 (አምስት መቶ ብር)
  • opening dateበዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks , Agricultural Products

የደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ/ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት የምግብ እህል በቆሎ እና ስንዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ/ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት የምግብ እህል በቆሎ እና ስንዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ለመጫረት የምትፈልጉ፡-

  1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፡ በዘርፉ የተሰማራ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና በ2018 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፡ ከገቢዎች ሚኒስቴር ወይም ከሚመለከተው የታክስ ባለሥልጣን የተሰጠ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፡ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።
  4. የድርጅት ምዝገባ ሰርተፊኬት፡ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (Commercial Registration Certificate) ማቅረብ የሚችል።
  5. የመንግሥት ግዥ ተሳታፊነት (Suppliers List) ፡ በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን የአቅራቢዎች ዝርዝር (Suppliers List) ላይ የተመዘገበ ለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል።
  6. የግብር ግዴታ ማረጋገጫ (Tax Clearance)፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘመኑ የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።
  7. የውክልና ማረጋገጫ፡ ተጫራቹ ድርጅቱን ወክሎ የሚጫረት ከሆነ ሕጋዊ እና በውል ማስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ ማቅረብ የሚችል።
  8. የመልካም ሥራ አፈጻጸም (Good Performance Certificate): ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ የመንግሥት ወይም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የምግብ እህል አቅርቦት በተሳካ ሁኔታ ማከናወኑን የሚያሳይ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።
  9. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security/CPO): ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስም በማዘጋጀት በቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ውስጥ አስገብቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. የሰነድ መሸጫ ዋጋ፡ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በአካውንት ቁጥር 1000521691305 በማስገባት የባንክ አድቫይስ ይዞ በመምጣት በዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ሰነድ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ናሙና አቀራረብ (Sample Submission) ፡ ተጫራቾች የበቆሎ እና የስንዴ ለእያንዳንዱ 50 ኪ.ግ የታሸገ የድርጅቱ ሎጎ ወይም ምልክት ያለው ናሙና በጨረታው ወቅት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ በስራ ቀን 15ኛው ቀን ድረስ የደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የጨረታ ዶክመንቶች በመግዛትና በዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ቴክኒካል ኦርጅናል 1 እና ኮፒ 1 ፋይናንሻል ኦርጅናል 1 እና ኮፒ 2 በድምሩ 5 ፖስታ የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ በአንድ እናት የጨረታ ፖስታ ውስጥ በማስገባት የደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዶክመንት ላይ በመፈረም ማህተም በማድረግ በፖስታ ጀርባው ላይ በሚታይ ጽሑፍ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት የያዘ ፖስታ ለይቶ መጻፍ አለበት፡፡
  14. የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
  15. በጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ሌሎች የመወዳደሪያ ነጥቦች (መስፈርቶች) በጨረታ ዶክመንቱ መሠረት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
  16. ተጫራቾች unconditional letters (በሁኔታ ላይ ያልተገደበ ደብዳቤ) ከታወቀ ባንክ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  17. በጨረታ ማስታወቂያ እና ዶክመንቱ ላይ የተገለፁትን የመወዳደሪያ ነጥቦችን ያሟላ ተጫራች ብቻ ወደ ድህረ ግምገማ ያልፋል፡፡
  18. ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቦታው ላይ ያለመገኘት የጨረታ መከፈትን አያስተጓጉልም፡፡
  19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፦ በቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 0920925053

አድራሻችን፡- በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ ዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ ውስጥ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቢሮ ከጅማ ከተማ በስተደቡብ 145 ኪ.ሜ ከወላይታ ሶዶ ከተማ በስተምዕራብ 165 ኪሜ ርቀት ላይ በተርጫ ከተማ ይገኛል፡፡

የደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ/ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

✨ messages.ai_summary
The commission seeks bids for the open tender procurement of food grains—maize and wheat—for the 2019 budget year. Bidders must hold a valid trade license, TIN, VAT registration, commercial registration, and tax clearance, plus be listed on the government suppliers list. Samples of 50 kg bagged grain with company logo are required.
Save Tender