የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት የከባድ ተሽከርካሪ መኪና መለዋወጫ እና የጋራዥ አላቂ ዕቃዎች ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ ፋ መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት የከባድ ተሽከርካሪ መኪና መለዋወጫ እና የጋራዥ አላቂ ዕቃዎች ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት-
1) የከባድ ተሽከርካሪ መኪና መለዋወጫ ግዥ -ሎት ምድብ 01/2019
2) የጋራዥ አላቂ ዕቃዎች-ሎት ምድበ 02/2019
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በሥራ መስኩ ሀጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው:
2. የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
5. ከሚመለከተው መ/ቤት የታከስ ከሊራንስ ማቅረብ አለበት፣
6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮio (አሥር) ተከታታይ ቀናት ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ጠዋት 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር:- 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
