በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት በዋግ ኸምራ ሰቆጣ ከተማ ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዪን /ኃ/የተወሰነ፡፡
የሃገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት በዋግ ኸምራ ሰቆጣ ከተማ ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዪን /ኃ/የተወሰነ፡፡/ 10000/አስር ሺ ኩንታል ጥራት ያለዉ አፈርና ሌላ ባእድ ነገር የሌለዉ፤ያልነቀዘ፤ መድሃኒት ያልገባበት/የተበጠረ/ ጥራቱን የጠበቀ ንፁህ ስንዴ በባለ 50 ኪሎ ግራም የተዘጋጀ ስንዴ ተቋሙ በሚያቀርበው የሰንዴ ናሙና መሰረት ማቅረብ ከሚችል፤በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዘት ይፈልጋል ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል ፡፡
- በዘመኑ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለዉቸዉና የዘመኑ ግብርን የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና (የምትችል)
- በግልጽ ጨረታ ከሚገዛዉ/ሰብል ጋር የተዛመደ ንግድ ስራ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት(Vaiue Aded Tax Certificate) ተመዝጋቢ የሆኑ /የግብር ከፋይነት ምስከር ወረቀት(Tax Payer Identificain Number) እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው የሚጠቀሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል (የምትችል )
- ተጨራቾች በግልጽ ጨረታ የሚገዛው ሰንዴ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ብር በመከፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 10 / አስር / ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ ሰቆጣ ከተማ ወይብላ ማሪያም አጠገብ ከሚገኘው ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ተመስርቶ መወዳደር የማይቻል መሆኑንና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት እንዲሁም የውል ማስከበሪያ 10% በባንከ በተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ (C.P.O) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ዋስትናው ውል ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 25 ቀናት ፀንቶ ሊቆይ የሚችል መሆኑን መገንዘብ ይኖርባችዋል
- ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንከ በተፈቀደላቸዉ በታወቁ ባንኮች ዋስትና (C.P.O)) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2 %ፐርስት በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ (C.P.O) ወይም በሁኔታው ላይያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ /ዋናውን የገቢ ደረሰኝ /ከማወዳደሪያ ሃሳብ ጋር አብሮ ማስገባት ሲኖርባቸው በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበትን ቀን አንስቶ ለተከታታይ 10/ አስር /ተከታታይቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ስዓት ሰነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በከቀን /አስረ አደኛዉ ቀን / 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባችዋል
- የጨረታዉ ሰነድ ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋቢ ሁለገብ /የገ/ህ/ስ/ማ ሃላፊነቱ የተወሰነ ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በክ/አስራ አደኛው ቀን /ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት ከጥዋቱ 3፡00 ታሽገው ከጥዋቱ 3፡30 ጨረታው ይከፈታል፡፡ በጨረታ መከፈቻ ስርአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ አከፋፈት ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስረአት ተገዥ ይሆናሉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ለማሻሻል ወይንም ከጨረታው ለመውጣት የፈለጉ እንደሆነ የጨረታ ማወዳደሪያ ሀሳብ ለማቅረብ ከተሰጣቸው 3 ቀን /ሶስት ቀን በፊት) በፅሁፍ ሊያሳውቁ ይገባል ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባችዋል ፡፡
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዋቢ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማህበር ኃላፊነት የተወሰነ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334401173 /0941821789/0933214815 በመደወል ማግኘት ይችላሉ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት በዋግ ኽምራ ሰቆጣ ከተማ ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዪን /ኃ/የተወሰነ
✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of 10,000 quintals of clean, untreated, quality wheat in 50kg bags, per sample. Bidders need valid trade license, VAT registration, and tax clearance.
