Tender Detail

Tender Details


የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ


የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል መጀመሪያ ፍ/ቤት ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በኮ/መ/ ቁጥር 8360 በሰጠው ውሣኔ መሠረት በአክሲዮኑ በአቶ ባህሩ ጋረደው ወ/አማኑኤል ስም ተዝግበው የሚገኙትን 272 አክሲዮኖች በሀራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በሀራጁ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 25 ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዶቻችሁን በማቅረብ መጫረት ትችላላችሁ።

ተጫራቾች ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶች:

  1. በጨረታው ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በመሳተፍ መግዛት ይችላል።
  2. የአንድ አክሲዮን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1000 (አንድ ሺ) ነው።
  3. ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን አሲዮኖች ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ከጨረታው ቀን በፊት ቄራ መላቅ ህንጻ በሚገኘው የአሲዮኑ መስሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ በመገኘት ከሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሠነዶቹን በመውሰድ መሙላትና በሰም በታሸ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 06፡00 ሰዓት ድረስ በአክሲዮኑ አስተዳደር ክፍል ማስገባት አለባቸው።
  4. ጨረታው ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና የሚለከታቸው ታዛቢዎች በሚገኙበት በአሲዮኑ ጽ/ቤት ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተጫረቱትን አክሲዮኖች የመነሻ ጥቅል ዋጋ 1/4 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. አንድ ተጫራች ሌላ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ይችልም።
  7. ተጫራቾች ዜግነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ መንጃ ፍቃድ፣ ፖስፖርት ወይም ተቀባይነት ያለው ሌላ ማስረጃ ኮፒ እንዲሁም ድርጅቶች ከሆኑ የመመሥረቻ ጽሑፍ ወይም ተቀባይነት ያለው ሰነድ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  8. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት(15) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለአhሲዮኑ ገቢ ማድረግ አለባቸው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስላቸውም።
  9. በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ውጤቱ እንደታወቀ ለአhሲዮኑ ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  10. በሌሎች ሕጐችና በንግድ ህጉ የተደነገጉ ሕጐች ተፈፃሚነት አላቸው።
  11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 470 1282/0911 35 69 42 ደውለው መጠየቅይችላሉ።

ሕብረት ልኳንዳ ነጋዴዎች አ.ማ.

Save Tender