Tender Detail

Tender Details


የስደቶች ተመላሾች አገልግሎት የጽዳት ዕቃዎች የጽፍህት መሳሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮች ለመግዛት ይፈልጋል።


1.የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ በጨረአው ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ ለመሳተፍ  በአቅራዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸው ኡየሚያሳይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው።

2. የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ በመፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጥበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ገንዝዘብ ያዥ ቢሮ ወይም ሂሣብ ከፍለው በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ። ቅዳሜና እሁድ የመስሪያ ቤቱ የስራ ቀናት አደሉም።

3. ተጫራቾች ይህ የስራ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዱ ላይ የዕቃዎች ዋጋ ዝርዝር በመሙላትና የጨረታ ማስከበሪያ በማካተት በአገልግሎት ዋና መ/ቤቱ የግዥ የቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ ጠዋት 4፤00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ዋጋ ለሚሰጡባቸው ዕቃዎች ናሙና /Sample/ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የሚያቀርቡትን አጠቅላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላላሾች አገልግሎት Refugees and Returnees Service  በሚል የተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /Uncondtional Bank Guarantee / ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ማለትም ሐምሌ 03 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ  4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፤30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸ በተገኙበት ይከፈታል።

6. አገልግሎቱ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

                                           አድራሻ፦

                         የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

           ምስኪ ህንፃ ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል እደተጓዙ ወደ 

                     ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ

                              አዲስ አበባ 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፦ 011 813 21 93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

Save Tender