Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Sugar Industry Group (Omo Kuraz No 1 and 3 Sugar Factory) Office
  • Address አዲስ አበባ ካሳንቺስ, Phone: +251-913544731
  • Website
  • Deadline10 Oct 2024, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Construction Equipment And Machinery

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ፅ/ቤት ለተለያዩ ኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እና የተቀፅላ መሳሪያ ጥገና አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።


ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር LP/OT/002 1 & 3/2017 ዓ.ም

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 /ቤት ለተለያዩ ኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እና የተቀፅላ መሳሪያ ጥገና አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል

  1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ/አዲስ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን/ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ/መረጃ ማቅረብ አለባቸው
  2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት 230-600 ከሰዓት 700-1030 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት 230-600 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የጥገና አገልግሎት ቀጥሎ የተመለከተውን የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል

      ሎት-1 Spare part of Power Plus Bull Dozer D8SEX-15 ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ

      ሎት-2 Spare part of Power Plus Bull Dozer D65EX-15 ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ

      ሎት-3 Spare part of John Deere backhoe loader ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ

      ሎት-4 Spare part of  Shantu backhoe loader ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ

      ሎት-5 Spare part of Hyundai front loader ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ

      ሎት-6 Spare part of Shandong front loader ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ

      ሎት-7 Spare part of Power Plus Grader PP12G-VI ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ

      ሎት-8 Spare part of Power Plus Grader PPI40G-VI ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ

      ሎት-9 Spare part of Nardi Harrower ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ብቻ

  1. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው 30/1/2017 . ከቀኑ 800 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 30/1/2017 . ከቀኑ 830 ሰዓት ላይ ይከፈታል ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል
  2. የጥገና አገልግሎቱ የሚከናወነው በደቡብ/ምዕ/ኢት///መንግስት በማጂ ወረዳ እና በደቡብ ኦሞ ዞን በሰላማጎ ወረዳ የኦሞ ኩራዝ-3 ስኳር ፋብሪካ
  3. ጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 60 ቀናት ነው
  4. የጨረታው ማስረከቢያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ 90 ቀናት ነው

ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

ኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ

የግዥ ቡድን

አዲስ አበባ ካሳንቺስ በተለምዶ መናኸሪያ ተብሎ ከሚጠራው ወደ አዋሬ በሚወስደው መንገድ ከጨርጨር ስጋ ቤት ዝቅ ብሎ የፋብሪካው ማስተባበሪያ ቢሮ

የስልክ ቁጥር (አድራሻ) +251-913544731/+251910120628/

+251 930754814

አዲስ አበባ

 

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ /ቤት

Save Tender