በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን በራጴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት እስቴሽነሪ እና የጽሕፈት መሳሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን በራጴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት እስቴሽነሪ እና የጽሕፈት መሳሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት
ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያ
- ሎት 2 ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
በዚሁ መሰረት
1. በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያለው ያላት
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው/ያላት
3. ፍቃዱን በበጀት ዓመቱ ያሳደሰ /ሰች
4. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች
5. መልካም የስራ አፈጻጸም ያለው ያላት
6. የጨረታ ማስከበሪያ CPO 30,000 ብር ሰላሳ ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ ማቅረብ የሚችል፡፡
7. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ያሸነፉበትን ዕቃ ወይም እስቴሽነሪ ራጴ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል ፡፡
8. አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፈውን ዕቃ ጥራት ለመለየት በየሎቱ የዕቃውን ናሙና ማቅረብ የሚችል፡፡
9. አሸናፍ ድርጅት ዕቃዎቹ በመጋዘኑ ውስጥ ስለመኖራቸው ለማሳየት ፍቃደኛ መሆን የሚችል፡፡
10. የጨረታው ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ የሚችል፡፡
11. ከተራ ቁጥር 1-10 ድረስ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ሊያወዳድራችሁ የሚችለውን መረጃ በመያዝ ራጴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ የምትወሰዱ ስሆን ጨረታው ለ15 (አስራ አምስት ) ለተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾቹ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የከፈታው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓልቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 09-11-66-92-98/09-32-46-01-71
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጌዴኦ ዞን የራጴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
