Tender Detail

Tender Details


በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ ከአጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019ዓ.ም የስራ ዘመን የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ሎት 1.


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ ከአጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019ዓ.ም የስራ ዘመን የተለያዩ እቃዎችን በ1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ሎት 1. ቋሚ እቃ ኤሌክትሮኒክስ (6313) ሎት2. የደንብ ልብሶች (621) ሎት3. የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች (6212) ሎት 4. አላቂ የትምህርት እቃዎች (6215) ሎት5. የተለያዩ መሣሪያዎችና መጻህፍት (6219) ሎት6. ሌሎች አላቂ እቃዎች (የፅዳት እቃዎች) (6218) ሎት7. ቋሚ እቃዎች (6314) ሎት8. የህክምና እና የላብራቶሪ እቃዎች (የቤተ-ሙከራ) (6214) ሎት9. የህትመት ስራዎች (6213) ሎት 10. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና (6243)

  1. የጨረታው ቁጥር 01/2019 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
  2. ተጫራቾች ለአቅርቦቱ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ሰርተፍኬት እና የታክስ ከፋይነት ቲን ነምበር ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በየአንዳንዱ ሎት 200 ብር በመከፈል ዘወትር በኮ/ቀ/ከ/ከ/ወ/ጠ አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት ካራ ቆሬ ታክሲ ተራውን እንዳለፉ ወደ አጃምባ መውጫ ባለው መንገድ ብሎኬት ማምረቻው እንዳለፉ ባለው ቅያስ ወደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በት/ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው በቢሮ ቁጥር 03 ፋይናስ ክፍል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10(አስር) የስራ ቀናት እሁድና ቅዳሜን ሳይጨምር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 12፡30 ምሳ ሰአትን ሳይጨምር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መስጠት አይችልም፡፡
  6. ገዢው ለሚገዛው ግዢ 20% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፡፡
  7. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን (ፋይናንሻል) እና ፎቶ ኮፒውን (ቴክኒካል) ሰነዶች ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ (ቢሮ) ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት ከ02፡30-11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክፍት ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዛው ቀን ከጠዋቱ 04፡30 ይከፈታል፡፡
  9. የሚቀርበው የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የድርጅቱ ሀላፊ ስምና ፊርማ እንዲሁም አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% በሲፒኦ አስይዘው ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6 ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በጨረታ ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ የማብራሪያ ጥያቄ በፅሁፍ ከጨረታው መክፈቻ 2 ወይም 3 ቀናት በፊት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በት/ቤቱ ግዢ ክፍል የስራ ሂደት ቅሬታውን በፅሁፍ ማቅረብ ይችላሉ በዚህ ክፍል የማይፈታ ከሆነ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይችላሉ፡፡ የጨረታው ውጤት በተገለጸ 7 ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ያላቀረበ ተጫራች በውጤቱ እንደተስማማ ተቆጥሮ ከአሸናፊው አካል ጋር ውል ይፈፅማል፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት የግዢውን ውል ከፈረሙበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10 የስራ ቀናት እቃውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  15. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባትም ሆነ ለማጭበርበር የሚሞከር ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
  16. ማንኛውም ተጫራች ለሚያስገባቸው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  17. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 (13,200) ለሎት 2 (7,300) ለሎት 3 (7,400) ለሎት 4 (6000) ለሎት 5 (10,000) ለሎት 6 (7,000) ለሎት 7 (14,200) ለሎት 8 (7.500) ለሎት 9 (1600) ለሎት 10 (750) የጨረታ ማስከበሪያ የግድ በሲፒኦ መሰራት አለበት ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  19. በመንግስት የተደራጁ ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው ፅ/ቤት በሀላፊ የተፈረመ ደብዳቤ ብቻ ይዘው ሲመጡ ይስተናገዳሉ፡፡
  20. ነጋዴዎች ሳምፕል ለሚገቡ እቃዎች ሳምፕል እንዲያቀርቡ እና ለቋሚ እቃዎች በፎቶ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

አድራሻ፡- በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/11 አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት ካራ ቆሬ ታክሲ ተራውን አንዳለፉ ወደ አጃምባ መውጫ ባለው መንገድ ብሎኬት ማምረቻው እንዳለፉ ባለው ቅያስ ወደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በት/ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው በቢሮ ቁጥር 03 ፋይናስ ክፍል

ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for the purchase of various goods across 10 lots, including electronics, uniforms, stationery, educational materials, equipment, books, cleaning supplies, medical and laboratory items, printing services, and electronic repairs. Bidders must hold a valid trade license, pay taxes, and have VAT and TIN certificates.
Save Tender