የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች የመኪና ጎማ ግዥ እና የሞተር ሳይክል ጥገና አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ወዞፋ/ግ/03/17
የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች የመኪና ጎማ ግዥ ለመፈፀም ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱ ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የግዥ አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ሎት 1 |
የመኪና ጎማ ግዥ |
50,000 ብር |
|
ሎት 2
|
የሞተር ሳይክል ጥገና አገልግሎት ግዥ |
50,000 ብር
|
ስለዚህ ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደለ ንግድ ስራ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፊኬት፣ የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ (ቲን) ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ የንግድ ፈቃድ ኮፒ እና የማይመለስ ብር 200 ሁለት መቶ እየከፈሉ ከወላይታ ዞን ፋ/ኢ/ል መምሪያ 2ኛ ፎቅ ከቢሮ ቁጥር 3 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በመ/ቤቱ የገቢ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከኦሪጅናል የጨረታ ሀሳብ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የአንዱን ዕቃ ወይም አገልግሎት ዋጋ የሚያቀርቡበትን የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው ዋጋ መሙያ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በጨረታ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 19 መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና 1 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመምሪያው የጨረታ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት አስፈላጊውን ውለታ በመፈጸም ዕቃውን አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ድረስ በማቅረብ ገቢ ሲያደርግ ሲጨርስ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 551 2116 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
