Tender Detail

Tender Details

  • Company የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (FDRE Refugees and Returnees Service)
  • Address የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ ከፌዴራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 813 21 93
  • Websitehttps://rrs.et/
  • Deadline01 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 200 (ሁለት መቶ)
  • opening dateበዚያው ዕለት 4፡30
  • Categories Vehicle , Vehicle Battery , Vehicle tire

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለሚገለገልባቸው ተሽከርካሪዎች የተለያዩ መለዋወጫዎችን፣ ጎማዎችን እና ባትሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለሚገለገልባቸው ተሽከርካሪዎች የተለያዩ መለዋወጫዎችን፣ ጎማዎችን እና ባትሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች፡-

  1. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ፣ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸውና በጨረታው ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  2. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም ሂሳብ ከፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የመስሪያ ቤቱ የስራ ሰዓት አይደሉም፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተጠቀሱት ዕቃዎች የፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዶችን ለየብቻ በማዘጋጀት በአገልግሎቱ ዋና መስሪያ ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የተጫራቾች ዋጋ በግልፅ የሚነበብና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለበት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ስራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የሚቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (Refugees and Returnces Service) በሚል የተዘጋጀ የባንክ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ ውል በሚፈርምበት ወቅት የመልካም ስራ አፈፃጸም ማስከበሪያ /Performance Bond/ እቃዎቹን ለማቅረብ ያሸነፈበትን አጠቃላይ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (Refugees and Returnees Service) በሚል በተረጋገጠ የባንክ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ ጥሪው በደረሰው በዐ ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መስሪያ ቤት ቀርቦ የስራ ውል መፈረም አለበት፡፡
  8. አሸናፊው ጥሪ በደረሰው በአስር ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መስሪያ ቤት ቀርቦ ውል ካልፈረመ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  9. አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ ከፌደራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር: 09-97-23-66-31/09-43-01-29-44

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

✨ messages.ai_summary
Procurement of spare parts, tires, and batteries for vehicles used by the Refugees and Returnees Service via open tender. Bidders must be VAT-registered, hold valid trade licenses, professional competence certificates, and supplier registration. Financial and technical documents must be submitted separately.
Save Tender