Tender Detail

Tender Details


የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለራሱና አገልግሎት ለሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎችና ተ/ጽ/ቤቶች፡-የተለያዩ እቃቆች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የሰ/ወ/ዞገ/መ/ግ/ጽ ጨረታ ቁጥር 001

 

የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለራሱና አገልግሎት ለሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎችና ተ/ጽ/ቤቶች፡-
1. ሎት 1 የጽ/መሳሪያ
ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ሎት 3 የመኪና እቃዎች
4. ሎት 4 የመኪና ጎማና ባትሪ
5. ሎት 5 የጽዳት እቃዎች
6 ሎት 6 ፈርኒቸር/የቢሮ መገልገያ እቃዎች/ የወጭ
7 ሎት 7 ፈርኒቸር /የቢሮ መገልገያ እቃዎች/የሀገር ውስጥ
8 ሎት 8 የተሽከርካሪ የሞተር ዘይትና ቅባት
9 ሎት 9 አጠቃላይ ዓመታዊ የህትመት ስራ
10. ሎት 10 አጠቃላይ የኤሌከትሮኒክስ ጥገና ስራ
11. ሎት 11 የፈርኒቸር (የቋሚ እቃ) ዓመታዊ ጥገና ስራ

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ለመሣተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟማላት ይጠበቅባቸዋል

1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው
3 በአዲሱ የንግድ ፈቃድ አሰራር መሰረት የQR ደረሰኝ ያሳተሙ /ማቅረብ የሚችሉ
4. የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ
5. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ማንኛውንም ዕቃ በአርጅናል መሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጭየማጓጓዣ የማስጫኛ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደ እስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በሰሜን ወሎ ዞን ግዥ ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፎቶ ኮፒና የፋክስ ቀለሞች ኦሪጂናል ስለመሆናቸው በሚወስደው ፕሪንተር - ማስሞከር፣ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በባለሙያ ማስፈተሽ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀን ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉትን እቃ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም፡ ስምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገፁ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር እና ታከስን ያካተተ ዋጋ መሆን አለበት፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናል እና ኮፒ በማድረግ በየሎቱ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9 ውድድሩ በድምር ዋጋ /በሎት/ መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ከ1 እስከ 11 ላሉት ሎቶች ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
11. ሎት 3 /የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች በመምሪያው የተሽከርካሪ እንክብካቤ ባለሙያዎች እና በጋራዥ ባለሙያዎች በጥምር የጥራት አረጋጋጭ ተፈትሾ የሚገባ ስለሆነ በየተሽከርካሪ ሞዴሎቹ ትኩረት ተሰጥቶ ኦርጂናል እቃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
12. ከሎት 9 -11 የህትመት ስራ፣ የኤሌከትሮኒከስ ጥገና እና የፈርኒቸር ጥገና ስራ ተጫራቾች የስራ ድርጅታችሁ በወልድያ ከተማ የተከፈተ ወይም ቅርንጫፍ ያላችሁ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
13. ተጫራቾች ከሎት 1- 11 ያሉትን የጨረታ ሰነድ መጫረቻ ሰነድ/ ከ 05/12/2018 እስከ 19/12/2018 ዓ.ም ድረስ በመምጣት ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
14. የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው በ20/12/18 ዓ.ም ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ከጧቱ በ4፡00 ታሽጉ በዚሁ ቀን 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ከሎት 7 እስከ ሎት 11 ያሉት ሎቶች ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታቸው በሌሉበት የሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዥ የመሆን /የመቀበል/ ግዴታ አለባቸው፡፡
15. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለመምሪያው ማሳወቅ አለባቸው::
16. የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት 1 እስከ ሎት 4 ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ከሎት 5 እስከ ሎት 8 ብር30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ከ ሎት 9 እስከ ሎት 11 ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክበተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1/በመ/ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ /ኦርጅናሉን/ በጨረታ ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
17. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ በሙሉ ሳያስረከቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም ሙሉ በሙሉ እንዳስረከቡ ከፍያው ወዲያውኑ ይፈጸማል፡፡
18. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም የተሳሳተ ስርዝ ድልዝ/የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል በህግም ያስጠይቃል፡፡
19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ማሳሰቢያ ፡-

·         ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0333311597 /2680 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ::
ከሎቱ አንድም ሆነ ከአንድ እቃ በላይ ዋጋ ያልሰጠ ተጫራች ካለ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡ ሳምፕል /ናሙና ታይቶ ዋጋ የሚሞላባቸውን እቃዎች ዝርዝር በዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሰረት የመ/ቤቱን ሳምፕል በማየት ዋጋ ሊሞላ ይገባል፡፡
ማንኛውም ተጫራች ግልጽ ያልሆነለትን ነገር ደውሎ ግልጽ ካልሆነለት በስተቀር ያለ አግባቡ ዋጋ መሙላት የለበትም፡፡
በኋላ ለሚያቀርበው ጥያቄ ተቋሙ የማይቀበልና የተቋሙ ሃሳብ ተቀባይነት ያለው መሆኑን እናሳስባለን::

 


የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
North Wollo Zone Finance Department seeks bids for 11 lots: office supplies, electronics, vehicle parts, tires/batteries, cleaning items, furniture, fuel/lubricants, printing, and maintenance services. Bidders need valid licenses, TIN, and VAT registration if applicable.
Save Tender