የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ለቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች አገልግሎት የሚውል የተለያየ መጠን ያላቸው ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ እና ዘይትና ቅባት ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ማ/ኢ/መ/ባ/- 02/17
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንገዶች ባለስልጣን ሰቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች አገልግሎት የሚውል የተለያየ መጠን ያላቸው
- በሎት አንድ ጎማዎች፣
- በሎት ሁለት ባትሪዎች፣ እና
- በሎት ሦስት ዘይትና ቅባት ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፤ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ መንግስት መ/ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾቾ በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ዋና እና አንድ ኮፒ የቴክኒካል ፕሮፖዛሉን ዋና እና አንድ ኮፒ በተሊያየ ፖስታ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ በተለየ ፖስታ ለብቻው በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከባለስልጣኑዋና መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ከፍት ነው።
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾቸ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዘንድ ዕውቅና ካላቸው የፋይናንስ ተቋም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ /C.P.O/ ለአንድ ጎማ ዓይነትና መጠን ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ብቻ ' ለአንድ ባትሪ ዓይነትና መጠን ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ ፣ ለቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች አገልግሎት የሚውል ለዘይትና ቅባት ደግሞ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በኢንሹራንስ ዋስትና የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም። እንዲሁም ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረሳል ለወደፊቱም መ/ቤቱ በሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
- ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ45 ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
የስልክ ቁጥር 011 365 9932
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም
ወልቂጤ- ኢትዮጵያ
