ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሆስፒታል የፅዳት ዕቃዎች፣ የሪኤጀንትና የህክምና ቁሳቁሶች፣ መድኃኒቶች፣ የሃይሩፍ መኪና፣ የጭነት መኪና፣ የህክምና ፎርማት ስራዎች እና የካፍቴርያ አገልግሎት ማቅረብ የሚችሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ ለማቅረብ ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ዋ/ዩ/ን/ኢ/መ/መ/ ሆስፒታል የሆስፒታሉ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
- 1ኛ ሎት(1) የፅዳት ዕቃዎች፣
- 2ኛ ሎት(2) የሪኤጀንትና የህክምና ቁሳቁሶች፣
- 3ተኛ ሎት (3) መድኃኒቶች፣
- 4ተኛ(ሎት 4) የሃይሩፍ መኪና፣
- 5ተኛ (ሎት 5) የጭነት መኪና፣
- 6ተኛ (ሎት 6) የህክምና ፎርማት ስራዎች፣
- 7ተኛ ሎት 7 የካፍቴርያ አገልግሎት ማቅረብ የሚችሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ ለማቅረብ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች፡-
- ከጨረታው ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- በግዢ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፤
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት (TIN NUMBER)፤
- በጨረታ የሚሳተፉበትን የንግድ ፈቃድ መስክ በምዝገባ የምስክር ወረቀት ውስጥ የተካተተ፤
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ግብር ከፋዮች ደግሞ ወርሃዊ የታክስ ማስታወቂያ በማቅረብ የሰበሰቡትን የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ገቢ ማድረጋቸውን የሚገልፅ ከፌዴራል ገቢዎች ባለስልጣን የተሰጠ ማረጋገጫ ደብዳቤ ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- የ2016 ዓ.ም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፤
ከተራ ቁጥር ከ1-7 ድረስ ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ፋይናንሻል ኦሪጅናልና ኮፒ እና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ በፖስታ በሰም በማሸግ በሆስፒታሉ ለጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ቢሮ ቁጥር 318 ግ/አስ የስራ ሂደት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በመግዛት የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በማስያዝ ጨረታውን በፖስታ ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡
ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሸጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ይሆናል፡፡
ሆ/ሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 046-1-78-07-11
P.O. Box:-22 Fax፡-2293
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ን/እ/መ/መ/ሪ/ሆስፒታል
