ፀደይ ባንክ (አ/ማ) ለአቶ ጌታቸው አባት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን በሰንጠረዡ የተዘረዘሩ መኖሪያ ቤቶችን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ (አ/ማ) ለአቶ ጌታቸው አባት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን በሰንጠረዡ የተዘረዘሩ መኖሪያ ቤቶችን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪ ስም |
የመያዣ ሰጪ ስም |
የካርታ ቁጥር |
ቤቱ የሚገኝበት ቦታ |
የቦታው ስፋትና የቤቱ ከፍታ |
የንብረቱ አይነትና አገልግሎት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
የጨረታ ቀንና ሰዓት |
ጨረታው የወጣበት |
|
|
1 |
ጌታቸው አባተ |
ቤዛ ጌታሁን |
የካ 253124/13 |
የካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 |
ስፋቱ 392 ካሬ ሜትር የቤቱ ከፍታ B+G+3 |
ለመኖሪያ |
64,430,886.94 (ስልሳ አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሠላሳ ሺህ ስምንት መቶ ሰማኒያ ስድስት ብር 94/100 ሳንቲም) |
9/03/2017 ዓ.ም |
ከጠዋቱ 3፡00 – 6፡00 ሰዓት |
ለሁለተኛ ጊዜ |
|
2 |
ጌታቸው አባተ
|
ጌታቸው አባተ |
ቦሌ 12/40/4/ 1/20892/10 731/01 |
በቦሌ ክ/ ከተማ ወረዳ 12
|
ስፋት 162 ካሬ ሜትር የቤቱ ከፍታ B+G+3 |
ለመኖሪያ |
30,761,523.91 (ሠላሳ ሚሊዮን ሰባት መቶ ስልሳ አንድ ሺህ አምስት መቶ ሀያ ሶስት ብር 91/100 ሳንቲም) |
10/03/2017 ዓ.ም |
ከጠዋቱ 3፡00 – 6፡00 ሰዓት |
ለሁለተኛ ጊዜ |
- ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ) በፀደይ ባንክ (አ/ማ) ስም በማሠራት ለጨረታ ማስካበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ፀድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ለ ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ከፍያዎች፤ ግብር፣ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላሉ፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀረው የሊዝ ክፍያ ገዥው ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
- ተጫራቾች ቤቶችን ኅዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ ለገሀር በሚገኘው የፀደይ ባንከ አ/ማ ዋናው መ/ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115584896 እና 0115581905 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
ፀደይ ባንክ
