ዳሽን ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የሚከተሉትን ተበዳሪ ወይም አስያዥ ንብረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ ይሸጣል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
የሐራጅ ቁጥር ዳባ/0034/26
ዳሽን ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የሚከተሉትን ተበዳሪ ወይም አስያዥ ንብረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ ይሸጣል፡፡
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
የአስያዥ ስም |
ለጨረታ የቀረበው ንብረት |
|
ጨረታው የሚካሄድበት |
|||||
| አገልግሎት | ከተማ፣ክ/ከተማ፣ወረዳ | የካርታ ቁጥር |
የቦታ ስፋት |
የጨረታው
መነሻ ዋጋው (ብር) |
ቀን |
ሰዓት |
|||||
| 1 | መላኩ ታምሩ ግዛዉ
|
ልደታ | ተበዳሪዉ |
ለመኖሪያ |
ሸገር ከተማ ፣
ኮዬ ፈጨ ክ/ከተማ |
OR0000709011034510001 | 41.96
ካ.ሜ |
1,924,492 | ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:00 – 6:00 | |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(C.P.O) በዳሽን ባንክ አ.ማ. በማሰራት በጨረታው ዕለት ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ ይካሄዳል፡፡
- የሐራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈለው ግብር፣ታክስ ፣ውዝፍ የሊዝ ክፍያ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) እና ሌላ ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ወጪዎችን ገዢው/አሸናፊው/ ይከፍላል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ የሰጠዉ ተጫራች በጨረታዉ አሸናፊ ነዉ የሚባለዉ ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰዉ ብቻ ነዉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑን ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያሲያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- በጨረታው ላይ አስያዥና ተበዳሪ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፤ ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሠዓት 10 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
- ጨረታው ተጀምሮ በተቀመጠው ሰዓት ውስጥ ካልተጠንቀቀ ሊራዘም ይችላል፡፡
- ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች አብርሆት ቤተ መጽሀፍት አካባቢ በሚገኘዉ ዳሽን ባንክ (አ.ማ) ሰሜን አዲስ አበባ ቀጠና ብድር ማስመለስ ክፍል በስራ ሰአት በመገኘት ክፍሉ በሚያመቻቸዉ ፕሮግራም መሰረት ንብረቱን መጎብኘት ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-704038 ወይም 0111-704953 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ዳሽን ባንክ አ.ማ.
