በአማራ ከልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለቡልጋ ከተማ አስተዳደር ዘላቂ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚውል የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ በዘርፉ የተሠማሩና በደረጃ 4 እና በላይ የሆኑ ህጋዊ ተጫራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል ፡፡
የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ከልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለቡልጋ ከተማ አስተዳደር ዘላቂ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚውል የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ በዘርፉ የተሠማሩና በደረጃ 4 እና በላይ የሆኑ ህጋዊ ተጫራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል ፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች መሥሪያ ቤቱ ባወጣው የፍላጎት ዝርዝር መግለጫ መሠረት አንድ 200 ሜትር ጥልቀት ያለው የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ ለማሠራት የሚፈልግ በመሆኑ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው ቴክኒካልና ፋይናንሽያል በሚል ተለይቶ አንድ ኦሪጂናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማቅረብ በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ ሲሆን ተጫራቾች
በጨረታው ለመሣተፍ ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች :-
- በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የታደሠ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው ፤
- የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /NAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሠማሩ ሆነው ደረጃ 4 እና በላይ መሆንና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡
- የቴከኒካል ብቃት ማጣሪያው አስፈላጊ መመዘኛዎች :- ሀ / የባለቤትነት / አሁን ያለ የኪራይ / የጉድጓድ መቆፈሪያ ማሽን ፣ ኮምፕረሰር….ለ/ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ተመሳሳይ ርቀት የቆፈረበት የሥራ ልምድ ሐ/ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮው የቡድን የሥራ ልምድ እንዲሁም ጠለቅ ያለ ተጨማሪ መረጃ ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ 1 እስከ 5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 12 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ 22ኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሠዓት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር / በመክፈል መግዛት ይቻላል ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / ቢድ ቦንድ / ብር 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሣ ሺህ ብር /በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / ሲ.ፒ.ኦ / ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ሥም ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / ቢድ ቦንድ / ለ60 ቀናት የሚቆይ ሆኖ መሰራት አለበት ::
- ተጫራች የጨረታ ሠነዱን በጥንቃቄ የቴክኒካልና የፋይናንሽያል በሚል ለየብቻው አንድ ኦሪጂናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል ::
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይችሉም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011-681-32-41/ 011-681-63-96 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ
ደ/ብርሃን
