Tender Detail

Tender Details


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለተለያዩ የሳይት ስራዎች ለመስራት የሚሆን የመቆፈሪያ ማሽን፣ ክሬን እና V 6 ሽፍን መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለተለያዩ የሳይት ስራዎች ለመስራት የሚሆን የመቆፈሪያ ማሽን፣ ክሬን እና V 6 ሽፍን መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት የሚገዛው እቃ አይነት ብዛት የጨረታ ማስከበሪያ ብር የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ጨረታው አየር ላይ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰአት የጨረታው መክፍቻ ቀን እና ሰአት
ሎት 1 የመቆፈሪያ ማሽን 01 1,000,000 ወከው02/2019 20(ለሀያ ተከታታይ ቀን) (በሀያኛው ቀን 8፡00 ሰአት) በኢትዮጵያ አቆጣጠር (በሀያኛው ቀን 8፡30 ሰአት) በኢትዮጵያ አቆጣጠር
ሎት 2 ክሬን 01 320,000
ሎት 3 V 6 ሽፍን መኪና 01 1,000,000

ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፋ-

  • የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር መቅረብ
  • ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ
  • የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት መቅረብ
  • የዘመኑ ግብር ግዴታ የተወጡ እና የከፈሉትን ማረጋገጫ መቅረብ የሚችል

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል ከወ/ከ/ው/አገ/ጽ/ቤት/ግ/ከ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች ከዚህ በላይ የቀረቡትን መረጃዎች ይዛችሁ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20(ሀያ ተከታታይ ቀናት) እስከ 8፡00 ድረስ ብቻ በወ/ከ/ው/አገ/ጽ/ቤት/ግ/ክ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ስታስገቡ ቴክኒካል 1 ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርጋችሁ እንድታስገቡ እንጠይቃለን፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በተገኘበት በሀያኛው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰአት በግልጽ ይከፈታል፡፡

ነገር ግን ሀያኛው ቀን በአል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታ እና ሰአት ይከፈታል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ 1. የተሞላው ዋጋ መግለጫ ካልተሰጠበት ከነቫት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ለበለጠ መረጃ 0911711864/0911710769

በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Worabe Town Water Service Office in Silte Zone, Central Ethiopia, seeks bids to procure a drilling machine, a crane, and a V6 pickup truck for various site works. Bidders must hold a valid business license, registration, tax clearance, VAT registration, and supplier registration certificate.
Save Tender