በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በ2017 በጀት አመት ከካፒታል በጀት ለመገንጠያ-ቁጠባ መንገድ ስራ እና ለኮሪደር ልማት ስራ አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ እቃዎችን ማለትም ሲሚንቶ፤ብረት፤ እና ተያያዥ ዕቃወችን በሎት/አንድ/፣ ድንጋይ ፣ አሸዋና ጠጠር የመሳሰሉትን በሎት2 /ሁለት/ እንዲሁም ቢቱሜን/ካርታሜ/ ፕራይም ኮት እና ቴርሞ ፕላስቲከ ቀለሞችን በሎት3 /ሶስት/ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በ2017 በጀት አመት ከካፒታል በጀት ለመገንጠያ-ቁጠባ መንገድ ስራ እና ለኮሪደር ልማት ስራ አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ እቃዎችን ማለትም ሲሚንቶ፤ ብረት፤ እና ተያያዥ ዕቃዎችን በሎት/አንድ/፣ ድንጋይ ፣ አሸዋና ጠጠር የመሳሰሉትን በሎት2 /ሁለት/ እንዲሁም ቢቱሜን/ካርታሜ/ ፕራይም ኮት እና ቴርሞ ፕላስቲከ ቀለሞችን በሎት3 /ሶስት/ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘመኑና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ ያለው
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ከገቢዎች የተጻፈ ማስረጃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ብር የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1.5% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣያ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በሚጠይቀው የዋጋ አሞላል ብቻ መሙላት አለበት ። በሚጠይቀው ዋጋ አሞላል ካልሞሉ የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይሆናል ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዝረዝር መግለጫ (ስፔስፊኪሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በሎት/በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከግ/ፋይ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 ማግኘት ይችላሉ።
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ8/02/2017 ዓ/ም እስከ 02/03/2017 ዓ.ም 11፡30 ድረስ መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ አንድ ቅጅ ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በግዥና/ፋይ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 3/03/2017 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖረባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በ 03/03/2017 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ 4:30 ላይ ይከፈታል፡፡ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻልን።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 351 33 37/033 551 05 04/ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ- የመስሪያ ቤቱ አድራሻ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ህንጻ አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 ላይ ነዉ።
በአ/ብ/ክ/መ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት
