የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ፍትሐብሔር ችሎት በድሬዳዋ ከተማ በቀበሌ 04 ክልል ውስጥ የሚገኘው የካርታ ቁጥሩ 3053 የሆነ ቤት እና ቦታ መነሻ ግምቱ ብር 1,118.098.33 /አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ ስምንት ሺህ ዘጠና ስምንት ብር ከ33/100/ በጨረታ አወዳድሮ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ላይ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ አቶ በቀለ ደሳለኝ ሀ/ጊዮርጊስ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ፀጋዬ ደሳለኝ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 93841 ስፋቱ 523 ካ/ሜ ያረፈ የተሰጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በድሬዳዋ ከተማ በቀበሌ 04 ክልል ውስጥ የሚገኘው የካርታ ቁጥሩ 3053 የሆነ ቤት እና ቦታ መነሻ ግምቱ ብር 1,118.098.33 /አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ ስምንት ሺህ ዘጠና ስምንት ብር ከ33/100/ ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም በጨረታ አወዳድሮ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡ ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 4፡00 ድረስ ባለው ጊዜ የተጫራቾች ምዝገባ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ የሚካሔድ ሲሆን ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ከጠዋቱ 4፡10 እስከ 5፡30 ባለው ጊዜ ይከናወናል። በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፉበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ በሞዴል 85 በፍ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ማስያዝ አለባቸው፡፡ ቀሪውን 3/4ኛ ገንዘብ ደግሞ ጨረታው በተካሔደ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ባይሆን ቀድሞ የተያዘው ገንዘብ ለጨረታ የወጣው ወጪ ተቀንሶለት ቀሪው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ፍትሐብሔር ችሎት
