የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለፖሊስ ኮሚሽኑ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የህክምና መገልገያ ዕቃዎች እና የተለያዩ መድሃኒቶች ለመግዛት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኦ/ፖ/ኮ ግ/ጨ/04/ 2017
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለፖሊስ ኮሚሽኑ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የህክምና መገልገያ ዕቃዎች እና የተለያዩ መድሃኒቶች ለመግዛት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ፖሊስ ኮሚሽኑ የሚገዛቸው ከዚህ በታች በሎት ተለይቶ ቀርበዋል፡፡ በዚሁ መሰረት የግዥዉ አይነት:- የተለያዩ የህክምና መገልገያዎች እና መድሃኒቶች
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ለውድድር ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% ሆኖ የሚያስዙት ዋስትና ከ500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ብቻ በባንከ የተረጋገጣ ሲፒኦ ወይም የባንከ ጋራንት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 (አስራ አምስት) ቀናት ከፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎችን በራሱ ወጪ የማጓጓዣ መጫኛ እና ማውረጃ ወጪዎችን ሸፍነው በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ግምጃቤት ድረስ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀነ ገደብ 30/03/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 30/03/2017 ዓ.ም በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አደራሽ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎችን ታክስ እንዲሁም ትራንስፖርት እና የመጫኛ እና ማውረጃ የጉልበት ማንኛውንም ወጭ ጨምሮ መሙላት አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የቀረበ ዋጋ ሁሉንም ወጪ አካቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
- ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አ/አባበ ክ/ከተማ ቂርቆስ ላንቻ አከባቢ
0913108990/0996054778
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን
