መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ልዩ ልዩ ለኮንስተራክሽን ግብዓቶች Stationary pump Truck Mounted Concrete Pump Mobile crusher. Mobile Mix Concrete. Baching Plant with Accessories, Mixing truck Roller,350 &750lt Mixer, vibrator, compactor, የጭነት ካሶኒ ፣ ሚስማሮች (ከ4 ቁጥር እስከ 15 ቁጥር እና የቆርቆሮ ሚስማር)፡ ባለ 28፡ 30፡ 32 እና 35 ጌጅ ቆርቆሮ፣ ኤጋ፣ የተለያዩ አጣናዎች (ማለትም ወራጂ ማገር ቋሚ : የግድግዳ ማዦር እና የቆርቆሮ ማገር ውፍረቱ ባለ 8፡10 እና 12)፣ ፕላይውድ፣ ሞራሊዮ፣ አር ኤች ኤስ ፡ ለህትመት የሚሆን ቲሸርት ከነቀለሙ ቀለም ወረቀት ከነ ቀለሙ፣ የባነር እና ስቲከት ሸራ ከነ ቀለሙ በተጨማሪም የተለያዩ የወጥ ጥራጥሬዎችና ቅመማ ቅመሞች፣ በርበሬ እንዲሁም የገላና የልብስ ሳሙና ማቅረብ የሚችሉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ በዘርፉ ያላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈለ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸውን ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ የሚያቀርቡትን ዋጋ የጨረታ ሰነዱን ከማዕከላችን ቢሮ 200 ብር በመክፈል ወስደው ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው:: ጨረታው ለ14 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በ15ኛው ቀን ዕሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0938707070/0940404040
ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
