በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የአየር ንብረት ማስተካከል የመሬት አያያዝ ፕሮግራም (CALM-P4R) በፕሮግራሙ በጀት ድጋፍ ለሚደረግላቸው ተጨማሪ 23 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች አገልግሎት የሚውሉ የላፕቶፕ ኮምፒውተሮችና ፕሪንተር ግዥ ቢሮ ባዘጋጀው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢት/ግቢ/ግጨ/04/2017
በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የአየር ንብረት ማስተካከል የመሬት አያያዝ ፕሮግራም (CALM-P4R) በፕሮግራሙ በጀት ድጋፍ ለሚደረግላቸው ተጨማሪ 23 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች አገልግሎት የሚውሉ የላፕቶፕ ኮምፒውተሮችና ፕሪንተር ግዥ ቢሮ ባዘጋጀው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ዘንድ ቢሮው ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ አግባብነት ያለው እና በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድና ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የግዥ መጠኑ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ከመሳተፍ ከላይ ከተራ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን የተገናዘቡ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
- የላፕቶፕ ኮምፒውተሮችና ፕሪንተር ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ :-
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን (በብር) |
|
1 |
ላፕቶፕ ኮምፒውተር |
ቁጥር |
50 |
85,000.00 |
|
2 |
ፕሪንተር |
ቁጥር |
1 |
በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ (የጨረታ ማስከበሪያ ለቢሮ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ ኮፒ በማያያዝ) ማቅረብ አለባቸው፤
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከ6/4/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 21/4/2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በአብከመ ግብርና ቢሮ ባህር ዳር ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በሁለት ፖስታዎች ማለትም በቴክኒካል ፖስታ እና በፋይናንሽያል ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የቴክኒካል ፖስታ መያዝ (ማካተት) ያለበት፤ የዕቃዎቹ ዝርዝር መግለጫ (specification)፣ በዘርፉ እና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርቲፊኬት፣ የማቅረቢያ ጊዜ፣ የማቅረቢያ ቦታ፣ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀንና የጨረታ ማስከበሪያ
-
- ፋይናንሽያል ፖስታ መያዝ /ማካተት/ ያለበት በዋጋ መሙያ ፎርም የተሞላ የእቃዎቹ ዋጋ ማቅረቢያ ብቻ ነው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ቅጅ (ኮፒ) በማዘጋጀት በፖስታው ላይ ዋና (ኦሪጅናል) ወይም ቅጅ (ኮፒ) መሆናቸውን የሚልጽ ጽሑፍ በፖስታው ካይ በማስፈርና በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ በግብርና ቢሮ የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ6/4/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 21/4/2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረበ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና ቢሮ የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በ21/4/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግብርና ቢሮ የግዥ/ፋይ/ንብ/ አስ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል ወይም በፋክስ ቁጥር +251-58-220-8771 በመላክ፤ በስልክ ቁጥር +251-58- 320-7115 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ /ባሕር ዳር/
