Tender Detail

Tender Details


የካራማራ የመ/ደ/ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለ2019 ዓ.ም ለመማር ማስተማር የሚውሉ የጽዳት ዕቃዎች፤ ለአስተዳደር ሰራተኞች የደንብ ልብስ፤ የእስቴንሸነሪ እቃዎች፤ አላቂ የትምርት ግብአቶች፤ ቋሚ የቢሮ አቃዎች /ፈርኒቸር/ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


መጀመሪያ ግዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የካራማራ የመ/ደ/ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለ2019 ዓ.ም ለመማር ማስተማር የሚውሉ የጽዳት ዕቃዎች፤ ለአስተዳደር ሰራተኞች የደንብ ልብስ፤ የእስቴንሸነሪ እቃዎች፤ አላቂ የትምርት ግብአቶች፤ ቋሚ የቢሮ አቃዎች /ፈርኒቸር/ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች በየዘርፉ የተሰማራችሁ ተጫራቾች በመሆናችሁ መረጃ እንዲያቀርቡ እንጋብዛለን፡፡

የጨረታ ዓይነቶች (ሎቶች)

  • ሎት1 የደንብ ልብስ
  • ሎት2 አላቂ የቢሮ ግብአቶች
  • ሎት3 የጽዳት እቃዎች
  • ሎት4 የህከምና እቃዎች
  • ሎት5 አላቂ የትምህርት ግብአቶች
  • ሎት6 ለጥገና የሚውሉ ግብአቶች
  • ሎት7 ኤሌከትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት8 ቋሚ የቢሮ እቃዎች (ፈርኒቸር)
  • ሎት9 ኮምፒዩተር ጥገና
  • ሎት 10 ህትመት ስራዎች

የተጫራቾች መመዘኛዎች

  1. ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስተር ባዘጋጀው የእቃ እና የአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግብር የመከፈል ግዴታቸውን የተወጡ እና የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው መረጃ የሚያቀርቡ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር /300/ ሶስት መቶ ብር ለእያንዳንዱ በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ዘወትር የስራ ሰዓት ካራማራ የመ/ደ/ት/ቤት የፋ/ግ/ን/አሰ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር በሎት የተቀመጠ ሲሆን፤ በእስቴሺነሪ አላቂ የጽፈት መሳሪያዎች /የምትወዳደሩ /5000/ አምስት ሺህ ብር በደንብ ልብስ የምትወዳደሩ /5000/ አምስት ሺህ ብር በጽዳት አቃዎች የምትወዳደሩ /5000/አምስት ሺህ ብር ቋሚ እቃዎች ፈርኒቸር/የምትወዳደሩ /10,000/ አስር ሺህ ብር የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች 10,000/ አስር ሺህ ብር አላቂ የትምህርት ግብአቶች ላይ የምትወዳደሩ /5000/ አምስት ሺህ ብር የህከምና እቃዎች ላይ የምትወዳደሩ /3000/ሶስት ሺህ ለጥገና የሚውሉ ግባአቶች ላይ የምትወዳደሩ /4000/አራት ሺህ ብር ኮምፒውተር ጥገና ላይ የምትወዳደሩ /5000/ አምስት ሺህ ብር የህትመት ስራዎች ላይ የምትወዳደሩ /3000/ ሶስት ሺህ ብር /CPO/ በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ፡፡
  6. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚጫረቱበት ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በከኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ በግልፅ ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል /ናሙና/ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
  9. መ/ቤቱ ለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ጀርባ ወረዳ 04 ጽ/ ቤት አለፍ ብሎ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0111235982 ወይም 0111268654

ካራማራ የመ/ደ/ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር

✨ messages.ai_summary
Open tender for supplying cleaning supplies, uniforms, stationery, educational materials, furniture, electronics, and more across 10 lots for Karamara School. Bidders need valid licenses, tax clearance, and VAT registration. Samples required.
Save Tender