ድርጅታችን አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ቤተሰቦች ቤት እድሳት አገልግሎት የሚውል 570 (ኣምስት መቶ ሰባ) ባለ 35 ጌጅ አንደኛ ደረጃ የጣሪያ ቆርቆሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች በትምህርት፣ በጤና እና በወጣት ልማት ዘርፎች በርካታ የልማት ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው።
ድርጅታችን ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ቤተሰቦች ቤት እድሳት አገልግሎት የሚውል 570 (ኣምስት መቶ ሰባ) ባለ 35 ጌጅ አንደኛ ደረጃ የጣሪያ ቆርቆሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፤
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 2% በባንከ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ወይም /Tin Number/፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው ወይም ከተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ነፃ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች፣
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 /ሰባት/ የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍለ ሃገር አውቶቡስ ተራ አዲሱ ሚካኤል አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ /መረጃ/ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር ከፍለው በመግዛት የምትሸጡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ አስገብታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ድርጅቱ ይጋብዛል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ8ኛው ቀን ከጧቱ 3:00 ላይ ተዘግቶ ከጧቱ 4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ስምንተኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ የሚቀጥለው ሰኞ ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ይሆናል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ - ስልክ - 011-213-18-29, 011-276-35-39, 09 96 23 09 27
አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት
