በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በ2017 በጀት ዓመት ለተቋማችን ግብዓትና አገልግሎት የሚውሉ ከታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሔራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ፡- አግጨ/009/አኩስፋ-2/2017
- በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በ2017 በጀት ዓመት ለተቋማችን ግብዓትና አገልግሎት የሚውሉ ከታች የተዘረዘረውን፡-
(በጥቅል 1) የእሳት አደጋ መኪና መለዋወጫዎች
(ጥቅል 2) የነዳጅ ቦቴ መለዋወጫዎች ግዥ
(ጥቅል 3) የሎቤድ መለዋወጫዎች
(ጥቅል 4) የሀይ ቤድ መለዋወጫዎች ጨረታ በብሔራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀን የባንክ ዋስትና /BID BOND/፣ በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር /Supplier List/ ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡ : የጨረታውን መክፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ይቀመጣል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት 2፡00-6፡00፤ ከሰዓት 7፡00-10:30 እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት፤ ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ በተመለከተው ነው::
- ኦሞ ኩራዝ ቁጥር -2 ስኳር ፋብሪካ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ፡ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞርያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነኣ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር :-09-17-82-65-84/09-40-20-94-64/09-38 30 91 60
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ጥቅል ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተመሠከረለት የ90 ቀን ሲፒኦ (CPO) ወይም በቅድመ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና /BID BOND/ ብር ለእያንዳንዱ ጥቅል 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዕቃው ርክክብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ መጋዘን ነው፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይባት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው።
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር - 2 ስኳር ፋብሪካ
