ብርሃን ባንክ አ.ማ. ከዚህ በታች ሞዴላቸዉ የተገለጹትን ተሽከርካሪ አዳዲስ መለዋወጫዎች ለማንኛም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የመለዋወጫ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ፋ/አ-09/17
ብርሃን ባንክ አ.ማ. ከዚህ በታች ሞዴላቸዉ የተገለጹትን ተሽከርካሪ አዳዲስ መለዋወጫዎች ለማንኛም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ለሽያጭ የቀረቡት መለዋወጫዎች ተሸከርካሪ ሞዴል ዝርዝር |
|
1 |
ቢሾፍቱ ፒካፕ |
|
2 |
ሃይዉንዳይ ኢን |
|
3 |
ሃይዉንዳይ ቫን |
|
4 |
ኪያ ፒካንቶ |
|
5 |
ኪያ ሪዮ |
|
6 |
ሊፋን 520 |
|
7 |
ቶዮታ ኤክስኪዩቲቭ |
|
8 |
ቶዮታ V 8 |
|
9 |
ዞታይ |
|
10 |
ግራትዎል ፒካፕ |
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡት መለዋወጫዎች ዝርዝር እና ብዛታቸው፣ የጨረታ መነሻ ዋጋቸዉ ለጨረታ በተዘጋጀዉ ሰነድ በዝርዝር ተቀምጧል።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ፣ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ መሳድኦ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ከፕሮፐርቲ እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- መለዋወጫዎቹን ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት ባቡር መጨረሻ በተለምዶ ሰማያዊ ሕንፃ ተብሉ የሚጠራዉ ሕንጻ ባለበት በኩል በስተቀኝ ባለዉ መንገድ ወደ ዉስጥ ገብተዉ የግብርና ምርት ማሳደጊያ አቅራቢ ድርጅት ሕንፃ አጠገብ በሚገኘዉ የባንኩ መጋዘን በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ሊገዙት ያሰቧቸዉን መለዋወጫዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በብርሃን ባንክ ስም የተዘጋጀ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች መለዋወጫዎች ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ CPO ጋር በማያያዝ በታሽገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥር 22 ቀን 2017 ዓም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ እና ሎጂስቲክስ መምሪያ ቢሮ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታዉ ጥር 22 ቀን 2017 ዓም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድካ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸዉን መለዋወጫዎች ባቀረቡት ነጠላ ዋጋ መሰረት በአጠቃላይ ብዛቱ ተባዝቶ ጠቅላላ ዋጋዉን በመክፈል አሽናፊነታቸዉ በተገለፀላቸዉ በአስር ቀን ዉስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
- ጨረታው ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን የመሰረዝ መብት አለዉ።
በስልክ ቁጥር 011 443 7439/011 663 1729/
011 618 2624/011 650 6480 ደዉለዉ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ
