Tender Detail

Tender Details

  • Company የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ፍትሐብሔር ችሎት
  • Address ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline22 Feb 2025, 8:45 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ፍትሐብሔር ችሎት በድሬዳዋ ከተማ በቀበሌ 04 ክልል ውስጥ የሚገኘው በካራማራ ሣይት የቤት ቁጥሩ A-132 የሆነ ቤት በጨረታ አወዳድሮ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ላይ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በፍ/ባለመበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ አዱኛ ቡልቡላ ቆሪቾ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 96398 የተሰጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በድሬዳዋ ከተማ በቀበሌ 04 ክልል ውስጥ የሚገኘው በካራማራ ሣይት የቤት ቁጥሩ A-132 የሆነ ቤት መነሻ ግምቱ ብር 872,571.60 /ስምንት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሰባ አንድ ብር 60/100/ እንዲሸጥ የታዘዘ በመሆኑ ነገር ግን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቤቱን በመያዝ ያበደረው ብር 865,982.07 /ስምንት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሁለት ብር 07/100/ እዳ ያለበት የካቲት 15 ቀን 2017 . በጨረታ አወዳድሮ በሀራጅ መሸጥ አስፈልጓል፡፡ ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2:45 እስከ 4:25 ድረስ ባለው ጊዜ የተጫራቾች ምዝገባ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ የሚካሔድ ሲሆን ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ከጠዋቱ 4:30 እስከ 5:30 ባለው ጊዜ ይከናወናል፡፡ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የማያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፉበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ በሞዴል 85 በፍ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ማስያዝ አለባቸው፡፡ ቀሪውን 3/4 ገንዘብ ደግሞ ጨረታው በተካሔደ 15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ባይሆን ቀድሞ የተያዘው ገንዘብ ለጨረታ የወጣው ወጪ ተቀንሶለት ቀሪው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ሊገነዘቡ ይገባል።

 

የድሬዳዋ ምድብ የፌ////ቤት ፍትሐብሔር ችሎት

 

Save Tender