ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በሎት በመከፋፈል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NVI 02/2017
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በሎት በመከፋፈል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1. አልሙንየም በሮችና ፖርትሽኖች አቅርቦት ገጠማ
ሎት 2. የኢፖክሲ አቅርቦትና ቅብ
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ሕጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ሠርተፍኬት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው መጀመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በሎት በመክፈል ከኢንስቲትዩቱ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተያያዘው ዋጋ ማቅረቢያ ፎርም መሰረት በመሙላት የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጀምሮ እስከ ጥር 26/2017 ዓ/ም ድረስ የኢንስቲትዩቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 27/2017 ዓ.ም በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋም ሆነ በሌላ የጨረታ ጉዳይ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ሎት 1 እና ሎት 2 ተጫራቾች በቦታው ድረስ በመምጣት የሚሠራውን ሥራ በመመልከት ትክክለኛውን ልኬት በባለሙያ መውሰድ አለባቸው።
- ለሎት 1 እና 2 አቅርቦትና አገልግሎት ግዥው 25% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ቢሾፍቱ ከተማ ከመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ አለፍ ብሎ ከእንስሳት ሕክምና ፋኩልቲ አጠገብ፤ ለበለጠ መረጃ ለማግኘት
011-433-83-39/09-12-22-98-61 መጠየቅ ይችላል።
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት
