በደ/ኢት/ያ በወላይታ ዞን በባይራ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በልማታዊ ሴፍቲ-ኔት ፕሮግራም-5 በካፒታል በጀት በተለያዩ ቀበሌያት ለሚሰሩ የመጠጥ ውሃ መስመር ዝርጋታን ለማከናወን የፋብሪካ ውጤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢት/ያ በወላይታ ዞን በባይራ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በልማታዊ ሴፍቲ-ኔት ፕሮግራም-5 በካፒታል በጀት በተለያዩ ቀበሌያት ለሚሰሩ የመጠጥ ውሃ መስመር ዝርጋታን ለማከናወን የፋብሪካ ውጤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ሎት 01 የፋብሪካ ውጤቶች 2. ሎት 02 የማዕድን ውጤቶችን፣
በመሆኑም በጨረታው ለመሣተፍ የምትችሉ ተጫራቾች ፡-
- በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በፌዴራል ግዥና የመንግስት ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፣
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዶከመንቱ በየሎት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ ፋይ/ስ/ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስ/ር የንግድ ፈቃዳቸውን ዋናውን ኦርጅናል/ በመያዝ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ጥሬ ብር ሲፒኦ /10,000/ አስር ሺህ ብር/ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ብቻ
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ኦርጅናልንና ሁለት የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ በባ/ኮ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፤
- የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ለ30 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4:30 ሰዓት በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ ፋይ/ስ/ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፤
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ሰርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፤
- ተጫራቾች በሚሠሩበት አካባቢ ምንም ዓይነት ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0956445021/0935782116 ደውስው ማነጋገር ይቻላል፡፡
የባይራ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
