ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ በሎት -1 የተለያዩ የቀላል እና የከባድ መኪና ጐማዎች፤ በሎት -2 የተለያዩ የቀላል እና የከባድ መኪና መለዋወጫዎች፤ እና በሎት -3 የፈረስ ጉልበታቸው 140 እና ከዚያ በላይ የሆነ ትራክተር ከነማረሻው እና ተቀጽላ ማረሻ ኪራይ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ቁጥር: ጣበስፋ/አግ/ብግጨ/05/2017
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ፤
በሎት -1 የተለያዩ የቀላል እና የከባድ መኪና ጐማዎች፤
በሎት -2 የተለያዩ የቀላል እና የከባድ መኪና መለዋወጫዎች፤
በሎት -3 የፈረስ ጉልበታቸው 140 እና ከዚያ በላይ የሆነ ትራክተር ከነማረሻው እና ተቀጽላ ማረሻ ኪራይ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ በ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ/ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተራ ቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂ. ቁጥር 1000057735167 በመክፈልና የባንክ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ. 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው፡
አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘንአ ሆስፒታል አካባቢ
የፌደራል ቤቶች ኮርፖረሽን ህንጻ፡፡
ብሎክ A ቢሮ ቁጥር B008
ስልክ ቁጥር 011 5-586725 /0912031748
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡
- የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011558-67-25/0912031748 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
