የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚገኝ ፋብሪካ ነው። ፋብሪካው የተለያዩ መጠን ያላቸውን የፕላስቲክ ምርቶችን (UPVC Pipes, HDPE Pipes, Green House Sheet and Geomembrande Sheet) የሚያመርት የመንግሥት የልማት ድርጅት ሲሆን በፋብሪካው ግቢ በተመረጡ ቦታዎች ብዛት 09 CCTV (Closed-circuit television) ካሜራዎችን መትከል ይፈልጋል፡፡
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር APF/15/2017/Local
የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚገኝ ፋብሪካ ነው። ፋብሪካው የተለያዩ መጠን ያላቸውን የፕላስቲክ ምርቶችን (UPVC Pipes, HDPE Pipes, Green House Sheet and Geomembrande Sheet) የሚያመርት የመንግሥት የልማት ድርጅት ሲሆን በፋብሪካው ግቢ በተመረጡ ቦታዎች ብዛት 09 CCTV (Closed-circuit television) ካሜራዎችን መትከል ይፈልጋል፡፡ ግዥው
- የካሜራዎችን አቅርቦት፡
- ለተከላ ሥራው የሚያስፈልጉ የኤሌክትሪክ ኬብሎችን፣ የፕላስቲክ ራኮችን እና ሌሎች ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን አቅርቦት
- ከላይ የተገለፁትን አቅርቦቶች እስከ ፋብሪካው ድረስ ማጓጓዝን፣
- ካሜራዎችን ሥራ ላይ ለማዋል ያለውን ማንኛውንም ዓይነት የሙያ ሥራ (Installation Work) እና
- ስለካሜራዎች አጠቃቀም እና መረጃ አያያዝ ስልጠናና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ሁሉ ያካትታል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች -
- ለ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፡ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN) Certificate እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ማለታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው የፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 103 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ሠነዱን በኢ-ሜይል ለሚገዙ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡ አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ቅርንጫፍ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013149996 ኢ-ሜይል አድራሻ:- amharapipefactory@gmail.com
- የጨረታ ማስከበሪያ ተወዳዳሪ ድርጅቱ ለተወዳደረበት ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በፋብሪካው ስም በማሰራት ማቅረብ አለበት
- የሕጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ኮፒ እና የዕቃዎችን ዝርዝር የቴክኒክ መስፈርት በኣንድ ላይ (Technical Bid Offer) በማለት ለብቻው ከዋጋ ማቅረቢያው (Financial Bid Offer) በመለየት በፖስታ በማሸግ (ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ማህበር
