አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈፅሞባቸው ከደንበኞቹ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች እና ኩባንያው ሲገለገልባቸው የነበሩ ቀላል ተሽከርካሪዎች ፣ ቁሳቁሶችንና ሌሎችንም ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈፅሞባቸው ከደንበኞቹ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች እና ኩባንያው ሲገለገልባቸው የነበሩ ቀላል ተሽከርካሪዎች ፣ ቁሳቁሶችንና ሌሎችንም ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- በመሆኑም እነዚህን ዕቃዎች ለመግዛት የምትፈልጉ ሁሉ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆያ ቃሊቲ ከሸገር ዳቦ ጎንና ቃሊቲ ኪዳነ ምህረት ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት ወይም ህብረት ኢንሹራንስ የተጎዱ ተሸከርካሪዎች ማቆያ ጀርባ የኩባንያችን ሪከቨሪ በመገኘትና በማየት የምትገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከየካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብሔራዊ ትያትር ጀርባ በሚገኘው አዋሸ ታወርስ የኩባንያው ዋና መ/ቤት እንግዳ መቀበያ ድረስ በመቅረብ የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው መጋቢት 06 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ቃሊቲ ከሸገር ዳቦ ጎን በሚገኘው የኩባንያችን ሪከቨሪ ይከፈታል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የመነሻ ዋጋቸው እስከ 5,000 ለሆኑት ብር 500፣ ከብር 5,001 እስከ ብር 10,000 ለሆኑት ብር 2,000 ከብር 10,001 እስከ 50,000 ለሆኑት ብር 5,000 ፣ ከብር 50,000 በላይ ለሆኑት የመነሻ ዋጋውን 10% /አስር በመቶ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ሁሉም የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒአ (CPO) መቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች ከተዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ ውጪ ሞልተው የሚያቀርቡት ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ከጨረታው በኋላ ያሉትን ወጪዎች በሙሉ ገዢው ይሸፍናል፡፡
- አሸናፊዎች ንብረቶቹን ጨረታው ከተካሄደበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ክፍያውን ፈጽመው ካልተረከቡ ጨረታው የሚሰረዝ ከመሆኑም በላይ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ አይደረግም፣ በሌላ በኩል ክፍያ ፈፅመው ዕቃዎቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ቢሆን ኩባንያው ኃላፊነት የለበትም፡፡
- በአዋጅ ቁጥር 681/2010 አንቀፅ 6 (3) በተደነገገው መሠረት በጥገና ለሚከናወንባቸው ተሸከርካሪዎች የተሸከርካሪው የባለቤትነት ስም እንዲዛወርለት በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ለሚመለከተው የመንግስት መስሪያ ቤት ማመልከት ይኖርበታል፡፡
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- ዋና መ/ቤት፡- 011 557 00 01 / የሪከቨሪ:- 011 439 11 01/
ፋክስ :- 011 557 02 08
አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ
