በደቡብ ኢት/ያ ክልል በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሁለተኛ ጊዜ የእንስሳት መድሃኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢት/ያ ክልል በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሁለተኛ ጊዜ የእንስሳት መድሃኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የምችሉት በሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና ለ2017 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ከዚህ በፊት ላከናወናቸው ተመሳሳይ ሥራዎች (አገልግሎቶች) ከአሠሪው አካል የመልካም ሥራ ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ ብር) በሶዶ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት መደበኛ አካዉንት ቁጥር 1000018212335 ገቢ ያደረጉበትን ስሊፕ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት ቢሮ ይገኛል።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 16ኛው ቀን የበአላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና የ20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በታወቀ ባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ርክብክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ይሆናል፡፡
- የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 091 685 6313/091 634 9825/ 091 079 2939 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ::
በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳደር
ፋይናንስ ጽ/ቤት
