Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት
  • Address , Phone: 0118279123
  • Website
  • Deadline12 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 1000 (አንድ ሺ ብር)
  • opening date16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Categories Health Care, Medical Industry , Pharmaceutical Products , Medical Equipment And Supplies

በአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት የጅምላ ንግድ አከፋፋይ አገልግሎት የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

 

በአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሁሉም /ከተሞች ጤና መድኅን ተጠቃሚዎች ለፌዴራል ጤና መድኅን ተጠቃሚዎች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድኃኒቶች እና የህክምና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ 53 መድኃኒት ቤቶች እና የጅምላ ንግድ አከፋፋይ ድርጅቶች የዱቤ / credit እና የጥሬ ገንዘብ / cash ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የመንግሥት የልማት ድርጅት ነው፡፡ ስለሆነም ድርጅታችን ከነማ ፋርማሲ የጅምላ ንግድ አከፋፋይ አገልግሎት የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አምራች እና የመድኃኒት አስመጪ የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በንግድ ዘርፍ ወይም በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የቲን ማስረጃዎች፡

ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1000 (አንድ  ብርበመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ  15 ተከታታይ የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ) ጉለሌ /ከተማ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS /ኤስ ኤም ኤስ ኤስሕንፃ 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን 430 ሰዓት የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ሰለሆነ አርፍዶ የሚመጣ ተቀባይነት የለውም፡፡ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 430 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን በድርጅቱ ግዥ ዳይሬክቶሬት ክፍል 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 የሚከፈት ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡-

v ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

v ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ በዋለበት ቀን በዋና /ቤት ማስታወቂያ ቦርድ እንዲሁም በተለያዩ የበይነ መረብ አማራጮች በምናሳውቀው ቀንና ሰዓት መሠረት ከተጫራቾች ጋር የቅድመ ጨረታ ስብሰባ የሚካሄድ መሆኑን እንገልፃለን።

አድራሻ፡- ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚዎስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS / ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ሕንፃ 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403

የሥራ ሰዓት፡ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 200 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ከሰዓት 700 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 200 ሰዓት እስከ 600 ሰዓት

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-1-72-71-37

 

በአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት 

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of pharmaceuticals and medical supplies via wholesale distribution services. Eligible bidders are domestic manufacturers or importers with valid trade licenses and TIN.
Save Tender