Tender Detail

Tender Details

  • Company በምዕራብ ወስጋ ዞን መንዲ ዲስትሪክት ሆስፒታል
  • Address Oromia Ethiopia, Phone: ቁጥር 0917081440 እና 0931649752
  • Website
  • Deadline08 Sep 2026, 10:01 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር500 (አምስት መቶ)
  • opening dateከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Categories Printing And Publishing , Textile, Garment & Leather , Pharmaceutical Products

በምዕራብ ወለጋ ዞን መነሲቡ ወረዳ መንዲ ዲስትሪክት ሆስፒታል በ2019 የበጀት ዓመት ለሆስፒታሉ የሚያገለግሉ


የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕራብ ወለጋ ዞን መነሲቡ ወረዳ መንዲ ዲስትሪክት ሆስፒታል በ2019 የበጀት ዓመት ለሆስፒታሉ የሚያገለግሉ

  1. የተለያዩ ህትመት ውጤቶች፣ የተለያዩ መደሃኒቶች፡ ሪ-ኤጀንቶችን እና የሰራተኞች ደምብ ልብስ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች

  1. ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
  3. ግብር የመከፈል ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን ማስረጃ የሚያቀርብ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበት አይነት ለመለየት የማይመለስ ብር500 (አምስት መቶ) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚጫረቱበት አይነት ለእያንዳንዱ ቢዲቦንድ በሲፒኦ ብር 5000 (አምስት ሺህ) የጨረታ ሰነዱን ስያስገቡ ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  6. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚጨረቱበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገው ኤንቨሎፕ ውስጥ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት አየርላይ ይውላል። በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00-6፡00 ሰዓት በመንዲ ሆስፒታል ገንዘብና ፋይናንስ ሥራ ሂደት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጅው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  9. መሥሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0917081440 እና 0931649752 ደውሎ ይጠይቁ።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ ይሆናል፡፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ዲስትሪክት ሆስፒታል

✨ messages.ai_summary
Tender for Menti District Hospital in West Wollega Zone to procure printing materials, pharmaceuticals, reagents, and staff uniforms. Bidders must hold valid trade licenses, be VAT-registered, registered with the Ministry of Finance, and provide tax clearance certificates.
Save Tender