የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳዳር የፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ የስራ ሂደት በ 2017 በጀት ዓመት በወረዳ ውስጥ ለሚገኝ በበጀት ዓመቱ ለሚያከናውነው የእቃና አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በሎት /ምድብ የግዥ አይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/4/ፋ/ 002/17
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳዳር የፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ የስራ ሂደት በ 2017 በጀት ዓመት በወረዳ ውስጥ ለሚገኝ በበጀት ዓመቱ ለሚያከናውነው የእቃና አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በሎት /ምድብ የግዥ አይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1. አላቂ የቢሮ እቃዎች (ስቴሽነሪ) ግዥ
ሎት 2. የደንብ ልብስ ግዥ
ሎት3. የጽዳት እቃዎች ግዥ
ሎት4. ኤሌክትሮኒክስ ግዥ
ሎት 5. ቋሚ እቃ ግዥ
በመሆኑም መ/ቤታችን ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 በተዘረዘሩት የግዥ ምድቦች መወዳደርና መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች /አቅራቢ/ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
- የዘመኑ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ እና ተጫራቾች የተመዘገቡበትን ኮፒ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ተመዝጋቢዎች መሆን አለባቸው፡፡
- የሚቀርበው የዋጋ ሰነድ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት 1-5 ላሉት ለእያንዳንዱ ሎት በአድራሻችን ብር 10,000 /አስር ሺ ብር/ በCPO መቅረብ አለበት፡፡
- በስራ ክህሎት የተደራጁ ኢንተርፕራይዝ ከሆነ በተደራጁበት ዘርፍ ላይ ብቻ ልዩ ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲሆን ካደራጃቸው ጽ/ቤት ሀላፊ በተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከስራ ዘርፍ ውጭ ለሆኑት እንደማንኛውም ነጋዴ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለባቸው፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በየሎቱ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ከሎት 1-3 ለተገለጹት ዕቃዎች ሰነዱን በሚያስገቡበት ቀን ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡እቃው በናሙናው ላይ ያለውን የጥራት ደረጃ ይዞ ካልተገኘ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ገዢው አካል የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ለአሸናፊ ተጫራቾች በሰነድ ውስጥ የተካተተውን ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 10 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ 10% ሲፒኦ አሰርተው ውል መዋዋል አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሰፉባቸውን እቃዎች በወቅቱ ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረሳል፤ ተመላሽ አይደረግም፡፡
- የእቃ ማስረከቢ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 04 የፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ/ንብረት አስተዳደር ይሆናል።
- በሚቀርበው የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የድርጅቱ ሀላፊ ወይም ህጋዊ ውከልና ያለው ከውክልናው ደብዳቤ አያይዞ ስምና ፊርማ የድርጅቱ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለሚቆጠር 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ከፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 04 የፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ ስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- የዕቃ ማጓጓዣ ብር አሸናፊው ተጫራች ይሸፍናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት 11ኛው ቀን የእረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በተከታዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ በሚያስገቡበት ጊዜ ከመስሪያ ቤቱ የተሸጠላቸውን ሰነድ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር መመለስ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
አድራሻ ፡- ከአየር ጤና ወደ አለም ባንክ በሚወስደው መንገድ ከትሮፒካል ከፍ ብሎ ወረዳ 4 ህንጻ 1ኛ
ፎቅ ፋይናንስ ፅ/ቤት ለበለጠ መረጃ 011-8-33 84 81/ 011-369 37-20
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳዳር
የፋይናንስ ጽ/ቤት
