Tender Detail

Tender Details

  • Company Geda Transport and Logistics S.C. (ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲከስ አ.ማ)
  • Address ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮልጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 558 25 19
  • Websitehttps://www.gedatransport.com/#
  • Deadline04 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-04 00:00:00
  • Categories Vehicle Battery

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲከስ አ.ማ የተለያዩ የብረት ቁርጥራጮች ፤ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ባትሪዎች እና ፊልትሮዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር [Gada/NCB/08/2017]

 

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲከስ አ. የተለያዩ የብረት ቁርጥራጮች ያገለገሉ የተሽከርካሪ ባትሪዎች እና ፊልትሮዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች እና የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ወይም ያላት እና በማንኛውም ንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ወይም የተሰማራች
  2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12 ፎቅ ከጠዋቱ 230 እሰከ 1100 በመምጣት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም ወይም በመፈረም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አጠቃላይ የተወዳደሩበትን ዋጋ 2% ሲፒኦ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአንድ ላይ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ ሰነድ የገዙ ተወዳዳሪዎች የገዙትን ሰነድ እና ደረሰኝ በመያዝ እቃዎችን ሞጆ በሚገኘው የድርጅቱ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ማየት ይቻላል፡፡
  6. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት አጠቃላይ ያሸነፉበትን እቃ ሙሉ በሙሉ በመክፈል እቃውን ከጊቢ ማውጣት አለባቸው፡፡
  7. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም
  8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ 16ኛው ቀን 800 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 830 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ ሞጆ ይገኛሉ፡፡
  10. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ፤ ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12 ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፦ 011-558-25-19

 

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ..

 

Save Tender