በአብከመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ አስተዳደር የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በሸክላ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ጠቅላላ ስፋቱ 4780 /አራት ሺ ሰባት መቶ ሰማንያ/ ካሬ ሜትር የሆነ ለንግድ እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
የሶስተኛ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብከመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ አስተዳደር የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በሸክላ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ጠቅላላ ስፋቱ 4780 /አራት ሺ ሰባት መቶ ሰማንያ/ ካሬ ሜትር የሆነ ለንግድ እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች
- የጨረታውን ሰነድ በሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በመሬት ልማትና ባንክ ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ቦታው የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታውን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን /Specifection/ መሰረት መሆን ይኖርበታል፤፤
- ተጫራቶች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 10 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 10 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።
- ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በአ/ብ/ዞን በሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በመሬት ልማትና ባንክ ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን 11/7/2017 ዓ.ም እስከ 24/7/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ24/7/2017 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ25/7/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡
- ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ።
- የአካባቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
- የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ --በስልክ ቁጥሮች 0910245551 /0923661118 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት
